
ኤፕሪል 2 በዩኒቨስቲ ኦፍ ሜሪላንድ ሜዲካል ሴንተር ላይ አሁን በስራ ላይ ባሉና በቀድሞ ሰራተኞች በቀረበው ክስ ላይ እንደተዘረዘረው ከሆነ 80 የሚጠጉ የመስሪያ ቤቱ ሰራተኞች ለአስር አመት ያህል በገዛ ባልደረባቸው የስልክና ሌሎች አካውንቶቻቸውን በመስረቅ፤ እንዲሁም የመስሪያ ቤቱን ኔትወርክ በመጥለፍ በተለይም በሴት ባልደረቦቹ ላይ ያልተገባ ግለኝነት መብት የሚጋፋ ተግባር ሲፈጽም እንደከረመ ታይቷል።
ተጠርጣሪ የተባለው ማቲው ባቱላ በተለያዩ ጊዜያት የባልደረቦቹን ፓስወርዶችና ቁልፎች ከመስሪያቤቱ ኮምፒውተሮች በመስረቅ በርካታ ግላዊ የሆኑ መረጃዎችን ሊያገኝ ችሏል። ከነዚህም መኃል የባልደረቦቹን ኢሜይሎች፤ ቴክስት ሜሴጆች፤ ፎቶዎችና ቪዲዮዎችን የሰረቀ ሲሆን ያገኛቸውን የእርቃን ምስሎችና ቪዲዮችን ደሞ ዳውንሎድ በማድረግ እንዳስቀመጣቸው በክስ መዝገቡ ተተንትኗል።
አልፎ ተርፎም ሰራተኞች ለልጆቻቸው የጡት ወተት ፓምፕ በሚያደርጉበት ወቅት ጭምር የሆስፒታሉን የካሜራ ሲስተም በመጥለፍ ቪዲዮዋቸውን ሰርቋል።
ይህ ግለሰብ ከዚህ በተቸማሪ የባልደረቦቹን የቤታቸውን የሴኩሪቲ ካሜራ በመጥለፍ ልብሳቸውን ሲቀይሩ፤ ከቤተሰብጋ ሲጫወቱ አልፎ ተርፎም የግብረ ስጋ ግንኙነት ሲፈጽሙ ይመለከት እንደነበር ተገልጿል።
የተጎጂ ጠበቆች እንደሚሉት ዩኒቨርስቲው ይህ ወንጀል እንደተፈጸመ ከ2024 ጀምሮ ያውቅ እንደነበር ሆኖም ምንም አይነት እርምጃ እንዳልወሰደ በማስታወቅ ይህን ክስ እንደጀመሩ ተናግረዋል።
በዚህ ጉዳይ ተበድያለሁ የሚል ማንኛውም ሰው ግራንት ኤንድ አይዘንሆፈር የተባሉትን ጠበቆች እንዲያናግር ተመክሯል።

