12/12/2024

About

ይህ ድረ-ገጽ በዲሲ-ሜትሮ አካባቢ በተለያየ ስራ በተሰማሩ ኢትዮጵያውያን ተዝጋጅቶ በዋናነት በዲሲ፤ ሜሪላንድና፤ ቨርጂንያ ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የተለያዩ መረጃዎችን፤ መልካም አጋጣሚዎችን፤ የስራ ድሎችን፤ የቤት ኪራይና የቤት ባለቤትነት መብቶችን/አጋጣሚዎችን እና የመሳሰሉትን ወቅታዊና ጠቃሚ መረጃዎችን ለማጋራት ታስቦ በመስከረም 2021 ተጀምሯል። አላማችን በዲሲ-ሜትሮ አካባቢ ያሉ መልካም አጋጣሚዎችን ወደ አማርኛ በመተርጎምና በአንድ ድረ-ገጽ በማሰባሰብ በስራ ብዛት፤ በቋንቋ ችግርና በመሳሰሉት ምክንያቶች የሚያጋጥም የመረጃ ክፍተትን መድፈን ነው። በሂደትም በስልክ የታገዘ የነጻ ምክር አገልግሎትና ተመሳሳይ የማህበረሰብ ግንባታ አገልግሎቶችን በበጎ ፈቃደኞች ታግዘን እናቀርባለን።

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት