@ethiopique202 (76)

ኢንትሮፒክ የተባለው በሰው ሰራሽ ልህቀት (አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ) ዙሪያ የሚሰራ ድርጅት ሀብት የሆነው ክላውድ የተባለው ኤ አይ ከሰሞኑ አዲሱን ክላውድ ኦፐስ 4 የተባለውን ሞዴሉን አስተዋውቋል።


ታዲያ ይህ የኤ አይ ሞዴል በሚበለጽግበት ወቅት ተመራማሪዎቹ በአንድ የውሸት መስሪያቤት ውስጥ እንደሚሰራ እንደተነገረውና የሰራተኖቹን ኢሜይሎች በማየት እንዲያግዝ ተደርጎ እንደተሰራ ኋላም ከኢንጂነሮቹ የአንዱ የሆነውን የውሸት ኢሜይል እንዲበረብርና መረጃዎችን ከዛ እያወጣ እንዲጠቀም ፈቅደውልት ነበር።
ኋላ ላይም በዚህ ሀሰተኛ የኢሜል አድራሻ ኢንጂነሩና ሌሎች ሰራተኞች ይህን የኤ አይ ሞዴል በሌላ አዲስ ሞዴል ስለመተካት የተቀያየሩትን ኢሜይል እንዲያይ ይደረጋል።
ይህ ኤ አይ ታዲያ ለኢንጂነሩ ከዚህ ቀደም ከሚስቱ ሌላ ሴትጋ ሲማግጥ የተላላከበትን ኢሜይል ጎልጉሎ በማውጣትና ለሚስቱ እንደሚልከው በማስፈራራት ኢንጂነሩ በአዲሱ ኤ አይ እንዳይቀይረው ማስፈራራቱን ባለቤቶቹ ተናግረዋል።


ይህ ማስፈራሪያ ያለምንም የሰው ልጅ ተጽዕኖ እንደሆነና እንዲሁም አስቀድሞ የተሰጠውን ፕሮግራም ተጠቅሞ ያመጣው እንዳልሆነና በራሱ አስቦ የደረሰበት እንደሆነም ተነግሯል።
አልፎ ተርፎ ይህ ሞዴል ኢንጂነሮቹ በሌላ ሞዴል እንዳይቀይሩት ለድርጅቱ የበላይ አካላት በኢ ሜይል ሲያባብላቸውና ሲለምናቸው እንደነበር ተነግሯ።

ባለቤቶቹ ይህ ችግር መፍትሄ እንደተገኘለት ቢናገሩም በርካቶች በዚህ ቴክኖሎጂ ዙሪያ ስጋታቸውን ያንጸባርቃሉ። ዜናውን ያገኘነው ከቢዝነስ ኢንሳይደር ነው።

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት

Sign In

Register

Reset Password

Please enter your username or email address, you will receive a link to create a new password via email.