@ethiopique202 (77)

በዳውን ታውን ዋሽንግተን ዲሲ በተለይም ዘዋር (ወተር ፍሮንት) አካባቢ እድሜያቸው ከ18 አመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ከምሽት 5 ሰዓት ጀምሮ ብቻቸውን እንዳይገኙ ታዟል። የዲሲ ከንቲባ በመግለጫቸው ባለፉት ጥቂት ሳምንታት በመቶዎች የሚቆጠሩ ታዳጊዎች ዘ ዋርፍ አካባቢ በመገኘት የአካባቢውን ሰላም ሲረብሹ እንደነበርና አልፎ ተርፎም የተወሰኑት ወደ ዝርፊያ በመግባት በአካባቢው ያሉ የንግድ ተቋማትን የንግድ ስራ ሲያስተጓጉሉ እንደነበር አስታውሰዋል።
ይህንን ተከትሎም እኚህ ታዳጊዎች ከአርብ ሜይ 23 ጀምሮ እስከ ማክሰኞ ሜይ 27 ድረስ ከምሽት 5pm እስከ ንጋት 5am ድረስ ብቻቸውን መገኘት እንደማይችሉና ከወላጆቻቸውጋ ወይንም ዕድሜው ከ21 ዓመትና ከዛ በላይ ከሆነው ሰውጋ ብቻ መገኘት እንደሚፈቀድላቸው አስታውቀዋል።

ከከንቲባዋጋ አብረው መግለጫ የሰጡት የዲሲ ፖሊስ ቺፍ ፓሜላ ስሚዝ በበኩላቸው ፖሊሶቻቸው በብዛት በአካባቢው እንደሚገኙና አስፈላጊውን እርምጃ እንደሚወስዱ አስታውቀዋል።

የዲሲ ከንቲባ ሚውሪየል ባውዘር በበኩላቸው ለነዚህ ታዳጊዎች በባነከር የመዝናኛ ማዕከል የመዝናኛ ፕሮግራም እንደተዘጋጀና በዚህ ማዕከል በመገኘት በሙዚቃ፤ ምግብ እና ጨዋታዎች መዝናናት እንደሚችሉ አስታውቀዋል።

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት

Sign In

Register

Reset Password

Please enter your username or email address, you will receive a link to create a new password via email.