@ethiopique202 (30)

“እጃችሁን አንሱ” (Hands Off!) በሚል መርህ ቃል በመላው ዩናይትድ ስቴትስና በሌሎችም አገራት የፕሬዘደንት ትራምፕ አስተዳደርን የሚቃወም ህዝባዊ ሰልፍ ለኤፕሪል 5 የተጠራ ሲሆን የሰልፎቹ ማዕከል በዋሽንግተን ዲሲ እንደሚሆን ተነግሯል።

በመርህ ቃሉ መሰረትም ሰልፈኞች “ከሜዲኬይድ እጃችሁን አንሱ”፤ “ከሶሻል ሴኩሪቲ እጃችሁን አንሱ”፤ “ከስደተኞች እጃችሁን አንሱ”፤ “ከፍርድ ቤቶች እጃችሁን አንሱ” በሚሉ ሀረጎች ተቃውሟቸውን እንደሚያሰሙ ተነግሯል።
የሰልፉ አዘጋጆች በድረገጻቸው እንዳጋሩት ከሆነ የበጎ ፈቃደኛ ሰልፈኞች በእለቱ ከዩናይትድ ስቴትስ በተጨማሪ በኦስትሪያ ቪየና፤ በፖርቶ ፖርቹጋል፤ በፈረንሳይ በካልጋሪ፤ ካናዳና በሌሎች በርካታ ቦታዎች አዘጋጅተዋል።
በዲሲና አካባቢው ደሞ በዲሲ በዋሽንግተን ሀውልት አቅራቢያ ወይም በናሽናል ሞል፤ በቼቪ ቼዝ በዲሲና ሜሪላንድ ድንበር አቅራቢያ፤ በሲልቨር ስፕሪንግ ሜሪላንድ ኮልስቪልና ሀስቲንግስ ድራይቭ ላይ፤ እንዲሁም በበርተንስቪል፤ በኦልኒ፤ በማናሳስ፤ ባልቲሞር፤ ፍሬድሪክ ሜሪላንድና በመሳሰሉት ቦታዎች ይህ የተቃውሞ ሰልፍ ከእኩለ ቀን ጀምሮ ይደረጋል ተብሏል።
በዋሽንግተን ዲሲ የሚደረገውን የተቃውሞ ሰልፍ የሜሪላንድ ኮንግረስማን የሆኑት ጄሚ ራስኪን የሚመሩት ሲሆን በተጨማሪም የፍሎሪዳ ኮንግረስማን ማክስዌል ፍሮስት፤ የአሜሪካ የመንግስት ሰራተኞች ፌዴሬሽን ፕሬዘደንት ኤቨርት ኬሊ፤ እንዲሁም የሂውማን ራይትስ ካምፔይን ፕሬዘደንት ኬሊ ሮቢንሰን ንግግር ያደርጋሉ ተብሏል።

ሙቭ ኦን የተባለው ተቋም እንዳስታወቀው በዚህ በመላው አሜሪካ በሚደረግ የተቃውሞ ሰልፍ ላይ ከ250ሺህ በላይ ሰዎች ይሳተፉበታል ተብሎ እንደሚገመትና ፕሬዘደንት ትራምፕ ለሁለተኛ. ጊዜ ወደ ስልጣን ከመጡ ወዲህ ከተደረጉ ህዝባዊ ሰልፎች ሁሉ ትልቁ እንደሚሆን ተጠቁሟል።

ይህንን ተከትሎም የመንገድ መዘጋቶች፤ የህዝብ ትራንስፖርት መጨናነቆች ሊኖሩ እንደሚችሉና የዲሲና አካባቢው ነዋሪዎች ይህን ከግምት በማስገባት እንዲንቀሳቀሱ ተነግሯል።

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት

Sign In

Register

Reset Password

Please enter your username or email address, you will receive a link to create a new password via email.