በቨርጂኒያ ግዛት ፍሬድሪክስበርግ የሊ ሂል አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ውስጥ የሥስተኛ ክፍል ተማሪ መማሪያ ክፍል ውስጥ መሳሪያ ማምጣቱን ተክትሎ፤ ወላጆቹ በቁጥጥር ስር ውለው ክስ እንደተመሰረተባቸው የስፖትስልቫኒያ የፖሊስ ጽህፈት ቤት ገልጿል። ታዳጊው የጠዋት ስናክ ለመብላት እጁን ቦርሳ ውስጥ ከቶ በሚፈልግበት ሰዓት መሳሪያው መባረቁን ፖሊስ አስታውቋል። የፖሊስ ሃላፊ ሜጀር ኤሊዛቤት ስካት “መሳሪያ ታጣቂዎች እንዲህ ዓይነት ክስተት እንዳይፈጠር ጥንቃቄ ማድረግ አለባቸው” በማለት አሳስበዋል። ፖሊስ ሰኞ ዕለት ከጠዋቱ 11 ሰዓት በፊት በተፈጠረው ክስተት ማንም አለመጎዳቱን ገልጾ፤ ስፍራውን እየተጠበቀ ተማሪዎች ክፍሉን ለቀው መውጣታቸውን ገልጿል። የታዳጊው ሁለቱም ወላጆቹ የአምስት ሺህ ዶላር ቦንድ እንዲከፍሉና የፊታችን አርብ በስፖትስላቬኒያ ካውንቲ የታዳጊዎች እና የቤት ውስጥ ጉዳይ ፍ/ቤት እንዲገኙ ታዘዋል። የተማሪው መምህር ማንነታቸው ባይገለጽም በፍጥነት ተማሪዎቹን በማሰባሰብ እና ደህንነታቸውን በመጠበቅ ለወሰዱት እርምጃ ሙገሳ ተችሯቸዋል። ፖሊስ አስፈላጊው የምክር እና የማረጋጋት አገልግሎት ለሊ ሂል አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች መምህራን እና ወላጆች እየተሰጠ መሆኑም ገልጿል
ወንጀል
ኤፕሪል 2 በዩኒቨስቲ ኦፍ ሜሪላንድ ሜዲካል ሴንተር ላይ አሁን በስራ ላይ ባሉና በቀድሞ ሰራተኞች በቀረበው ክስ ላይ እንደተዘረዘረው ከሆነ...
ሰኞ ማርች 24 የዲሲ ካውንስል የፍትህና የህዝብ ደህንነት ኮሚቴ ዋና ሊቀ መንበር የሆኑት ብሩክ ፒንቶ ይፋ ባደረጉት ፒስ ዲሲ...
በቨርጂኛ የላውደን ካውንቲ ፖሊስ ሰኞ ፌብሯሪ 24 2025 እንዳስታወቀው በግምት ወደ 1 ነጥብ አራት ሚልየን ዶላር የሚጠጋ ገንዘብ ከአጭበርባሪዎች...
ከስር ያለው የቲክቶክ ቪድዮ እጅግ ሰቅጣጭ ምስል ስላለው ተጠንቀቁ:: የሚረብሻችሁ ከሆነ ባታዩት ይመከራል:: Graphic video below. Please proceed with...
የዲሲ ፖሊስ ትላንት ሰኞ ፌብሯሪ 3 2025 ባወጣው መግለጫ በዲሲ ሳውዝ ኢስት የተከሰተን የግድያ ወንጀል እያጣራ እንደሆነ አስታውቋል። ፖሊስ...
በፌርፋክስ ካውንቲ የፍራንኮኛ ፖሊስ ጣቢያ ዛሬ ማክሰኞ ፌብሯሪ 4 የወጣው ዜና እንደሚያሳየው በጃንዋሪ 27 ለሊት 2፡30am ላይ በ6700 block...
የትራምፕ ዋይት ኃውስ ትላንት እሁድ በኤክስ ገጹ ላይ ባወጣውና በአይስ በቁጥጥር ስር አውዬ ወደአገራቸው ዲፖርት አረጋቸዋለሁ ካላቸው ስደተኞች መኃከል...
ሐሙስ ጃንዋሪ 2 2025 – ዋሽንግተን ዲሲ ዛሬ ጧት 10 ሰዓት ላይ የካፒቶል ፖሊስ አባላት በዲሲ ዳውንታውን ፒስ ሰርክል...
ጋልቭስተን ስትሪት በሳውዝ ዌስት ዲሲ የ3አመት ህፃን ቤት ውስጥ በአግባቡ ሳይቆለፍበት የተቀመጠ ሽጉጥ አግኝቶ የአምስት አመት እህቱ ላይ በመተኮስ...