ከቨር-1-1

ኦገስት 18 2019 ረፋድ ላይ በ708 Kennedy Street ባለ መኖሪያ ቤት ቤዝመንት ውስጥ በተነሳ የእሳት ቃጠሎ ወቅት በተጠቀሰው ቤት በቤዝመንት ተከራይተው ይኖሩ የነበሩት የ40 አመቱ ፍጹም ከበደና የ10 አመት ታዳጊው ያፌት ሰለሞን ከአደጋው ለመዳን ከቤት ውስጥ መውጣት ባለመቻላቸው በአደጋው ለህልፈት ተዳርገዋል፡፡

የዲሲ መንግስት ታዲያ የቤት አከራዩን ለአደጋው ተጠያቂ ነው ሲል የከሰሰው ሲሆን በክስ መዝገቡ ላይ እንደሚታየውም አከራይ አደጋው ከመድረሱ በፊት ማርች 21 2019 ላይ ከዲሲ ፖሊስ በርካታ የቤት ህግ ጥሰቶች አሉበት በሚል ማስጠንቀቂያ ደብዳቤ ደርሶት ይነበረ መሆኑንና የዲሲ የማከራይት ፍቃድም እንደሌለው አሳውቀዋል፡፡ 

አከራይ ቤቱን በህገወጥ ሸንሽኖ ሲያከራይ እንደነበረ፤ አንዳንዶቹ ክፍሎች ፈጽሞ መስኮት እንደሌላቸው እንዲሁም የእሳት አደጋ መከላከያ ጭስ አነፍናፊ በቤዝመንት ጨምሮ በክፍሎቹ ውስጥ እንደሌለና ይህም ህገወጥ እንደሆነ አስረድተዋል፡፡ 

ይህን ተከትሎም የቤቱ አከራይ የሆኑት የ 67 አመት አዛውንት ጄምስ ጂ ወከር ዛሬ ፌብሯሪ 20 2025 በዋለው የከፍተኛው ፍርድ ቤት ችሎት ወንጀለኛ ተብለዋል፡፡ 

በዲሲ የፍጹምና ያፌትን ነፍስ በነጠቀው የእሳት አደጋ ወንጀለኛ የተባሉት የቤት አከራይ የ67 ዓመቱ ጄምስ ጂ ዎከር ከሰሞኑ በዋለው የዲሲ ችሎት ለ35 አመት የእስር ፍርድ አግኝተዋል። ይህ በፌደራልና በዲሲ አቃቤ ህጎች በጥምረት የተያዘ የክስ ፋይል ነበር።

እኚህ የ67 አመት አዛውንት የቤት አከራይ በቀረበባቸው የሁለተኛ ደረጃ የነፍስ ማጥፋት ወንጀልና በርካታ የንግድ ቤት ህግ ጥሰቶች የ35 አመት እስር የተፈረደባቸው ሲሆን በተጨማሪም የእስር ጊዜያቸውን ጨርሰው ሲወጡ ለ5 አመት በመንግስት ቁጥጥር ይደረግባቸዋል ተብሏል።

የዩ ኤስ የፍትህ ቢሮም እንደ ረዳት አቃቤ ህግ ነብዩ ፈለቀና የዲሲ እሳት አደጋ ባለሞያ ናሆም ተክሌን ጨምሮ በርካቶች ሌሎች በዚህ ጉዳይ ላይ በተለያየ ዘርፍ የተሳተፉ ባለሞያዎች አመስግነዋል።

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት

Sign In

Register

Reset Password

Please enter your username or email address, you will receive a link to create a new password via email.