
“ኑ ጭቃ እናቡካ” በሚል የተሰየመውና በአስር ሺዎች የሚሳተፉበትን የጎዳና ላይ ፕሮግራም በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ላለፉት ጥቂት አመታት ሲያዘጋጅ የነበረው ተቋም በሲልቨር ስፕሪንግ ሜሪላንድ ቅርጫፉን ከፍቷል።
በዚህ ቅርንጫፍ ተቋሙ ለልጆችና ለቤተሰብ የሚሆኑ ወርክሾፖችን፤ ባህላዊ ስነጥበብ ትምህርትና ስራዎችን፤ የሸክላ ስራ ልምምዶችን፤ እንዲሁም የቤተሰብ ፕሮግራሞችን እንደሚያዘጋጅ ኢትዮጲክ ያነጋገረቻቸው የተቋሙ መስራች አቶ ዮሴፍ አስታውቀዋል።

ከነዚህ በተጨማሪም ተቋሙ በዋሽንግተን ዲሲ ጆርጂያ አቬኑ ላይ ከሚገኘውና የዕውቁ የፊልም ባለሞያ ሀይሌ ገሪማ በሚተዳደረው ሳንኮፋ ቡናና መጻህፍት ሰኞ ሜይ 5 ምሽት “ፉት ኤንድ ፔይንት” የሚል የቡናና የስነጥበብ ምሽት አዘጋጅተዋል።
ኑ ጭቃ እናቡካ በኢትዮጵያውያን አርቲስቶቹ ሀመረ ሙሉጌታና በዮሴፍ ወልደአማኑኤል የተቋቋመ ድርጅት ሲሆን ከ2021 ጀምሮ እስካሁን ድረስ በአዲስ አበባ በርካታ ፌስቲቫሎችን፤ የልጆች የቴሌቪዥን ፕሮግራሞችንና ሌሎች አገልግሎቶችን ሲስጥ የቆየ ሲሆን አሁን ደሞ ወደ አሜሪካ በመምጣት ተመሳሳይ አገልግሎት ለመስጠት ተዘጋጅተዋል።

ተቋሙ በተጨማሪም ለልጆች ልደትና ለማንኛውም የልጆች ፕሮግራም የሚሆኑ የስነጥበብና አዝናኝ ፕሮግራሞች እንዳሉት አቶ ዮሴፍ የተናገሩ ሲሆን ሰዎች ስለተቋሙ መረጃ ለማግኘት ዋናውን ድረ ገጽ መጎብኘት እንደሚችሉና በአሜሪካ ስለሚኖራቸው ፕሮግራሞች ደሞ በቅርቡ ራሱን የቻለ ድረ ገጽ እንደሚኖር አስረድተዋል።

በሳንኮፋ ሰኞ ሜይ 5 በሚያዘጋጁት “ፉት ኤንድ ፔይንት” የተባለ ፕሮግራም ላይ ለመሳተፍ ከፈለጉ ወይንም ለተጨማሪ መረጃ ይህን ሊንክ ይጫኑ።