
ከስር ያለው የቲክቶክ ቪድዮ እጅግ ሰቅጣጭ ምስል ስላለው ተጠንቀቁ:: የሚረብሻችሁ ከሆነ ባታዩት ይመከራል::
Graphic video below. Please proceed with care.
—-
የዲሲ ፖሊስ ትላንት ረቡዕ ፌብሯሪ 19 በሰጠው በመግለጫ ከፖሊስ በተተኮሰበት ጥይት ለህልፈት የተዳረገው የ29 አመት ወጣት የሆነው ሱራፌል ዘሪሁን እንደሆነ አስታውቋል:: በመግለጫው እንደተቀመጠው ማክሰኞ ፌብሯሪ 18 ምሽት 6፡10 ላይ ሱራፌል በጆርጂያ አቬኑ ወደ ደቡብ መኪናውን ነድቶ በተቃራኒ መንገድ ላይ ካለ ከፖሊስ መኪናጋ ካጋጨ በኋላ ፖሊስ መኪና ውስጥ ያለውን የፖሊስ ባልደረባ ጩቤ እያሳየ ያስፈራራ ሲሆን ቀጥሎም ፖሊሱ መሳሪያውን እንዲሰጠው አስፈራርቶ ሳይሳካለት ቀርቷል፡፡ ፖሊስ ጉዳዩን ለማርገብ ከሹፌር መቀመጫ በመንሸራተት ወደ ተሳፋሪ መቀመጫ የሸሸ ሲሆን ሱራፌልን በተደጋጋሚ ጩቤውን እንዲጥል ጠይቆታል፡፡
ይህ ሁሉ እየሆነ አልመለስም ያለው ሱራፌል ላይ ታዲያ ፖሊስ የተኮሰ ሲሆን ተኳሹ ፖሊስ ከመኪናው ወርዶ የሆነውን ለማጣራት ሲሄድ ሱራፌል በድጋሚ ፖሊሱን እንደተጠጋው አክለው ገልጸዋል፡፡ ቀጥሎም 3500 block of Georgia Avenue NW ላይ ወዳለ ላውንድሮማት አቅራቢያ ወዳለ ሌላ ሲቪሊያን ወደሚያሽከረክረው መኪና በመሄድ ቀምቶ ለመሄድ እንደሞከረና ፖሊስ በዚህ ግዜ በተደጋጋሚ በመተኮስ እንደጣለው፡፡ በተደረገለት ምርመራም እዛው ህይወቱ እንዳለፈ እንደተረጋገጠ ፖሊስ አስታውቋል፡፡
በዚህ የተኩስ ልውውጥ የተሳተፉ የፖሊስ አባላት በአስተዳደራዊ ዕረፍት እንደሚገኙም የዲሲ ፖሊስ በመግለጫው አስታውቋል፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ ማንኛውም መረጃ ያለው ሰው በስልክ ቁጥር ደውሎ ጥቆማ እንዲሰጥ ፖሊስ አክሎ ጠይቋል፡፡ የፖሊስን ሙሉ መግለጫ ለማየት ከስር ያለውን ይጫኑ፡፡
ለመረጃው ራስ አስራትን እናመሰግናለን