@ethiopique202 (94)

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንሺያል ስኮላርሺፕ ፕሮግራም በ1964 በወቅቱ ፕሬዘደንት በነበሩት በሊንደን ቢ ጆንሰን አስፈጻሚ ትዕዛዝ የተቋቋመና በመላው ዩናይትድ ስቴትስ ላሉና በትምህርታቸው ከፍተኛ ልህቀት ላሳዩ ተማሪዎች የሚሰጥ የስኮላሺፕ ፕሮግራም ነው።

ተማሪዎች በዚህ ስኮላርሺፕ ለመመረጥ በትምህርታቸው እጅግ ጎበዝ መሆን አልያም በስነጥበብ ችሎታቸው ልቀው መገኘት ወይንም በመሪነት ብቃታቸው ልቀው መገኘት ይገባቸዋል።

በየአመቱም በዚህ መልካም ዕድል እስከ 161 ያህል ተማሪዎች ከመላው ዩናይትድ ስቴትስ ተወዳድረው የሚመረጡ ሲሆን በዘንድሮው ምርጫ ከሚቺጋን ግራንድ ብላንክ ኮሚውኒቲ ትምህርት ቤት ጆሹዋ ግርማ ተወልደ እና ከቴኔሲ ማርቲን ሉተር ኪንግ ጁኒየር የጤናና የኢንጂነሪንግ ማግኔት ሀይስኩል ደግሞ ሊና ዘውዱ ፈለቀ በእጩነት ወደግማሽ ፍጻሜ ተሻግረዋል።

የሚቺጋኑ ጆሹዋ ከአባቱ ግርማ ተወልደና ከእናቱ ናቱ እያሱ የተገኘ ሲሆን በዘንድሮው የትምህርት አመት የ12ኛ ክፍል ትምህርቱን በ4.47 ጂፒኤ ይመረቃል። ጆሹዋ
ጆሹዋ አባቱ ዶ/ር ርማ ተወልደ የኤሌክትሪካልና ኮምፒውተር ኢንጂነሪንግ በሚያስተምርበት በኬትሪንግ ዩንቨርስቲ ገብቶ ኮምፒውተር ኢንጂነሪንግ ለመማርና ኋላም በብሄራዊ የአገር ደህንነት ለመስራት ያስባል።

ጆሹዋ በግራንድ ብላንክ ትምህርት ቤት ቆይታው የሞዴል የተባበሩት መንግስታት ዋና ጸሀፊ በመሆን አገልግሏል። በተጨማሪም በትምህርት ቤቱ የክርክር ቡድን ውስጥ በአምበልነት፤ በፍሊንት የታዳጊዎች ኦርኬስትራ ደሞ በቫዮሊን ተጫዋችነት እንዲሁም በፈርስት ሮቦቲክ ውድድር ወቅት የቡድኑ ዋና ፕሮግራመር ሆኖ አገልግሏል።
ጆሹዋ የኮቪድ 19 ፓንደሚክ በገባበት ወቅት ከወንድሙጋ በመሆን በ20 ስቴቶች በሚገኙ የአዛውንቶች መጦሪያ ቤቶች ላሉ ነዋሪዎች ኮንሰርት እያዘጋጁ በዩቲውብና በዙም በመሳሰሉት ያዘጋጁ ነበር።

ይህንንም ስራቸውን ኋላ ላይ Using Technology as a Means for Musical Outreach to Nursing Home Residents የሚል የምርምር ስራቸውን እንዲሰሩ በር የከፈተላቸው ሲሆን የምርምር ስራቸውም ለህትመት በቅቷል።

ጆሹዋ ከአባቱጋ በመሆን በርከት ያሉ የምርምር ስራዎቹን ለህትመት ያበቃ ሲሆን ከነዚህም የተወሰኑትን በዚህ ሊንክ ያገኟቸዋል።

ሊና ዘውዱ ፈለቀ ደግሞ በቴኔሲ ከአባቷ ከአቶእ ዘውዱ ፈለቀ እና ከእናቷ ኤሚ አበበጋ የምትኖር ሲሆን በቴኔሲ በዘረ መል ምርምር ዘርፍ በሚደረግ የምርምር ውጤቶች ውድድር በተለይም ታይፕ ኤ ሲስቲንዩሪያ ለተባለው ስር የዘደደ የኩላሊት በሽታን በዘረ መል ቴክኖሎጂ ለማከም እንደሚቻል ያዘጋጀችው የምርምር ውጤቷ ለበርካታ ሽልማቶች አብቅቷታል።

ሊና የተበላሹ ወይንም ለህመም የሚያጋልጡ በሴሎች ውስጥ የሚገኙ የዘረመል አይነቶችን በመለየት ይህን ስር የሰደደ ይኩላሊት ህመም እንዴት ማከም እንደሚቻል እንዳሳየችና በዚህ ስራዋም የቴኔሲ ስቴት ሴኔት በስሟ ለክብሯ መታሰቢያ የሚሆን የመዘክር ሰነድ አውጥቶላታል።

ሊና በትርፍ ጊዜዋ በናሽቪል ቴኔሲ የኢትዮጵያ ማህበረሰብ ውስጥም የበጎ ስራ አገልግሎት እንደምትሰጥ ተናግራለች። አልፎ ተርፎም የማህበረሰቡን የታዳጊውች መማክርት ከሌሎችጋ ሆና እንዳቋቋመችና ለአንድ አመት ያህልም በፕሬዘደንትነት እንዳገለገለች ታውቋል።

ኢትዮጲክ ለነዚህ ታዳጊዎች መልካም ምኞቷን ከወዲሁ ትገልጻለች።

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት

Sign In

Register

Reset Password

Please enter your username or email address, you will receive a link to create a new password via email.