@ethiopique202-1

የቨርጂኒያ ግዛት የላውደን ካውንቲ የህዝብ ት/ቤቶች ቢሮ ራውንድ ሂል ኤለመንተሪ በተባለ ት/ቤት የአራተኛ ክፍል ተማሪ የሆነ ታዳጊ ፤ ከእሱ ጋር በተመሳሳይ እድሜ ባለች ሴት ተማሪ ላይ ጾታዊ ጥቃት ፈጽሟል ማለቱን ሰቨን ኒውስ ዘግቧል።

የታዳጊው ወላጆች ከመገናኛ ብዙሃን ጋር በነበራቸው ቆይታ ትምህርትቤቱ Title IX በመባል የሚታወቀው እና እ.ኤ.አ በ1972 የወጣው ማናቸውም የፌደራል ፈንድ የሚቀበሉ ት/ቤቶች ውስጥ ጾታዊ ጥቃት እና ማግለልን መከላከል ላይ ያተኮረውን ህግ፤ አለአግባብ ተጠቅመዋል በማለት ከሰዋል። ታዳጊው ለሦስት ቀናት ትምህርት ቤት እንዳይገባ ታግዶ የቆየ ሲሆን ክስተቱ በዘላቂነት የትምህርት መዝገቡ ላይ እየተጻፈ እንደሚዘልቅም ተገልጿል።

የታዳጊው ወላጅ እና የልጁን እንድሜ ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት “ከጾታ ጋር የተያያዘ ምንም ዓይነት እውቀት የለውም” ማለታቸው ተዘግቧል። በተመሳሳይ በህግ ሙያ ላይ የተሰማሩት አባቱም “እንደወላጅ ብቻ ሳይሆን እንደጠበቃም አስደንግጦኛል ብለዋል።”ወላጆቹ Title IX የተሰኘው ህግ አተገባበር በደንብ እስኪታይ ድረስም ጉዳዩን እንደማይተዉት አስታውቀዋል።

ከታዳጊው ጋር በተመሳሳይ የዕድሜ ክልል የምትገኘው ታዳጊ፤ ልጁ ከልብሷ በላይ መራቢያ አካላቶቿን መንካቱን ለወላጆቿ መናገሯን ተከትሎ ክሱ የተመሰረተ ሲሆን፤ በምርመራው ወቅት ታዳጊዋም የመጀመሪያ የክስ ሃሳቧን ማንሳቷን ብትገልጽም፤ የካውንቲው የትምህርት ቢሮ ‘ጾታዊ ትንኮሳ’ በሚል የተጀመረውን ክስ ‘ጾታዊ ትንኮሳን በመሞከር’ ወደሚል አሸጋግሮታል ሲሉ የታዳጊው ወላጆች ለመገናኛ ብዙሃን ተናግረዋል።

ወላጆች ለካውንቲው የትምህርት አስተዳደር ስለጉዳዩ ይግባኝ ቢጠይቁም፤ በጉዳዩ ላይ ውሳኔ ተደርሷል የሚል ኢሜል እንደደረሳቸውና፤ በእነሱ በኩል ያለው ነገር አለመታየቱን ወላጆቹ ተናግረዋል።

በተመሳሳይ ለምስክርነት ልጃቸው መጠራቷን የተናገሩት ወላጅ እናት ካውንቲው የልጃቸውን መልስ በሌላ ትርጉም በመውሰድ እንዲሁም የልጁን ንጽህና የሚያሳየውን የንግግሯን ክፍልም ቆርጠው በማውጣት ያልሆነ ውሳኔ ላይ በመድረሳቸው በከፍተኛ ሁኔታ እንዳሳዘናቸው ለመገናኛ ብዙሃን ተናግረዋል።

እኚሁ ወላጅ በመስክርነት የተጠቀሰችው ልጃቸው ድርጊቱ ሲፈጸም አለማየቷን በመግለጽ፤ የሰጠችው ምስክርነት ከመዝገቡ ውስጥ እንዲወጣ በስልክ እና በኢሜል ጠይቀውም ካውንቲው ምላሽ እንዳልሰጣቸውም ገልጸዋል።የ ታ ዳ ጊ ው ወ ላ ጅ እ ና ት ል ጆ ች በ ዚ ህ እ ድ ሜ ያ ቸ ው የሚያደርጓቸውን ነገሮች የወሲብ እና የጾታዊ መልክ መስጠትብትክክል አለመሆኑን ገልጸዋል። “በዚህ እድሜያቸው ገና ክፍል ው ስ ጥ እ ን ኳ ን የ ቤ ተ ሰ ብ ህ ይ ወ ት እ ና ጾ ታ ጉ ዳ ዮ ች አልተማሩም።

በዘጠኝ ዓመት እድሜው ማሰብ ያለበት ከጓደኞቹ ጋር እግር ኳስ ስለመጫወት፣ ነጻ ሆኖ ዋና ስለመዋኘት ነው” ያሉ ሲሆን ለልጃቸው ስለተከሰሰበት ጉዳይ ለማስረዳት የነበራቸውን ውይይት በህይወታቸው ካደረጓቸው በሙሉ ከባዱ እንደሆነም ተናግረዋል።

ታዳጊዎቹ የተለያየ ክፍል እንዲማሩ ምርጫ ቢሰጣቸውም ቀሪው የትምህርት ዘመን፤ አንድ ክፍል ውስጥ ለመማር መወሰናቸውን የተማሪው ወላጅ እናት መናገራቸው ተዘግቧል

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት

Sign In

Register

Reset Password

Please enter your username or email address, you will receive a link to create a new password via email.