@ethiopique202-1

ባሳለፍነው ሳምንት መጨረሻ ላይ የኢሚግሬሽን ፖሊሶች (አይስ) በካሊፎርኒያ ሎስ አንጀለስ ከተማ ንጋት ላይ ባደረጉት ያልታሰበ የጉልበት ፍተሻ የተነሳ፤ የካሊፎርኒያ ጎዳናዎች በተቃዋሚ ሰልፈኞች ተጨናንቀው ሰንብተዋል። ሰልፈኞቹ “ከአሁን በኋላ ድንገተኛ ፍተሻ አይኖርም” እና “ቤተሰቦቻችን በሰላም ይኑሩበት” የሚሉ ጽሁፍ ያለባቸው መፈክሮችን ይዘው ታይተዋል።

ሰልፈኞቹ በሰላማዊ መንገድ ተቃውሟቸውን ሲገልጹ ቢቆዩም፤ ይሁን እንጂ የፌደራል ባልደረቦች ከከተማዋ ህግ አስከባሪዎች ጋር በመሆን አስለቃሽ ጭስ መርጨት እና የጎማ ጥይት መተኮስ ሲጀምሩ ሁኔታው ወደ ግጭት ተሸጋግሯል። ይህን ተክትሎም ብዙዎች የታሰሩ ሲሆን አንድ ተቃዋሚ ተከሷል።

የካሊፎርኒያ ግዛት ሀገረ ገዥ ጋቪን ኒውሰም ሁኔታውን “ጨካኝ” ሲሉ የጠሩት ሲሆን፤ የፌደራል መንግስት በስደተኛው ማኅበረሰብ ዘንድ ስጋት እየፈጠረ ነው በማለት ወንጅለዋል።

ሀገረ ገዥው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከካሊፎርኒያ ግዛት ፍቃድ ውጭ 2000 የሚሆኑ ብሔራዊ ዘቦች እንዲላኩ ማዘዛቸውን ተክትሎ ስጋታቸው አይሏል።

ዋይት ኋውስ የፕሬዝዳንቱ እርምጃ በካሊፎኒያ እየተከሰተ ሲል የጠራውን “ስርዓት አልበኝነት” ለመዋጋት አስፈላጊ የሆነ እርምጃ ነው ብሏል። ይሁን እንጂ የካሊፎኒያ ባለሥልጣናት ሁኔታው ስደተኛው ማኅበረሰብ ዘንድ ስጋት ለመፍጠር ያለመ የፖለቲካ ጨዋታ ነው ብለውቷል።

በካሊፎርኒያ የተከሰተውን ሁኔታ ተከትሎ የሜሪላንድ ግዛት ዋና አቃቤ ህግ አንተኒ ብራውን ድንገተኛ እና ጉልበት የታከለበትን ፍተሻውን በመቃወም ከካሊፎኒያ ጋር በአጋርነት እንቆማለን በማለት ትላንት እሁድ ሰኔ ስምንት 2025 (እ.ኤ.አ) መግለጫ አውጥተዋል።

ዋና አቃቤ ህጉ “ህዝቦቻቸውን ከፌደራል መንግስት ከሚከላከሉ ከካሊፎኒያም ሆነ ከማናቸውን ግዛቶች ጋር አብረን እንቆማለን” ያሉ ሲሆን ማናቸውም የኢሚግሬሽን ጉዳይ አፈጻጸሞችም መሰረታዊ የሰብዓዊ መብትንም ሆነ የህዝብ ደህነንት በጣሰ መልኩ መሆን የለባቸውም በማለት አሳሰበዋል።

የስደተኞችን ሰብዓዊ አያያዝ በሚመለከት ልክ እንደ አቃቤ ህግ ብራውን ሁሉ በመላው ሀገሪቱ ያሉ 20 የሚሆኑ ግዛት አቃቤ ህጎችም በህብረት መግለጫ ያወጡ ሲሆን ፤ ሜሪላንድ የዚህ ጥምረት አንዷ ሆናለች። ምንም እንኳን በሜሪላንድ የካሊፎርኒያን ግዛት መሰል ሁኔታ ባይከሰተም የስደተኛ ጉዳይ ባለሞያዎች ግን ሁኔታው ስጋት እንዳጫረባቸው በመናገር ላይ ናቸው።

በሎስ አንጀለስ የጀመረው ተቃውሞ በተለያዩ የካሊፎኒያ ግዛቶች እየተቀጣጠለ ሲሆን በቀጣይ ቀናትም ተጨማሪ ሰልፎች እንደሚኖሩ ይጠበቃል። በአንጻሩ በሜሪላንድ የሚገኙ የስደተኛ

ጉዳይ ባለሞያዎች በዲሲ፣ ሜሪላንድ እና ቨርጂኒያ ግዛት ተመሳሳይ ሁኔታዎች እንዳይከሰቱ

ጥንቃቄ እና ትኩረት ያሻል በማለት አሳስበዋል

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት

Sign In

Register

Reset Password

Please enter your username or email address, you will receive a link to create a new password via email.