@ethiopique202 (91)

የዩናይትድ ስቴትስ ጠቅላይ አቃቤ ህግ የሆኑት ፓም ቦንዲ ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳሳወቁት ከዩናይትድ ስቴትስ በስህተት ዲፖርት የተደረገው ኪልማር አብሬጎ ጋርሲያ ከኤልሳልቫዶር ፕሬዘደንት ቡኬሌ ጋር በመተባበር ዛሬ ወደ ዩናይትድ ስትቴትስ እንዳስመጡትና በዩናይትድ ስቴትስም በተከሰሰባቸው የህገወጥ የሰዎች ዝውውር ወንጀል ለፍርድ እንደሚቀርብ ተናግረዋል።

የፌደራል አቃቤ ህግ ባለፈው ወር መጨረሻ ላይ ኪልማር አብሬጎ ጋርሲያን በሁለት ወንጀሎች እንደከሰሰውና ለአመታት ሰነድ አልባ ሰዎችን ከቴክሳስ ወደ መሀል አገር ሲያመላልስ ነበር ሲል ይከሰዋል። ይህንን ተግባር ለማከናወንም ከ100 በላይ ጉዞዎችን አከናውኗል ሲል የክስ መዝገቡ ያሳያል።

የተከሳሹ ጠበቃ ፍርዱ መታየት ያለበት መጀመሪያ ጉዳዩን የያዘው ዳኛጋ ነው ቢልም መንግስት ግን ክሱን በናሽቪል ቴኔሲ እንደሚያደርገው አስታውቋል። በዚህ ወንጀል ጥፋተኛ ከተባለ በያንዳንዱ አጓጉዞታል በተባለው ሰነድ አልባ ሰዎች አስር አስር አመት የሚፈረድበት እንደሆነም ተነግሯል።

ጠቅላይ አቃቤ ህጓ እንዳሉት ጋርሲያ ፍርዱን በዩናይትድ ስቴትስ ከጨረሰ በኋላ ወደ አገሩ ዲፖርት እንደሚደርረግ በመግለጫቸው አስታውቀዋል።

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት

Sign In

Register

Reset Password

Please enter your username or email address, you will receive a link to create a new password via email.