
በሜይ 22ና 23 ተመርተው ለገበያ የቀረቡና በአንድ ፓውንድ እሽግ የተዘጋጁት ኦርጋኒክ የተፈጩ ስጋ ምርቶችን የገዙ ሰዎች እንዳይጠቀሟቸው የአሜሪካ ግብርና ቢሮ የምግብ ደህንነትና ቁጥጥር ቢሮ አስታወቀ። ለዚህም ምክንያት ያላቸው ደሞ ይህ የተፈጨ ስጋ በውስጡ ኢ-ኮላይ የተባለ በሽታ አማጭ ጀርም በውስጡ ሊኖርበት እንደሚችል በመታመኑ ነው።
ይህ ምርት በላዩ ላይ ያለው ማስረጃ “1-lb. vacuum-packed packages of “ORGANIC RANCHER ORGANIC GROUND BEEF 85% LEAN 15% FAT” የሚል ሲሆን የመገልገያ ቀኑም እንደሚከተለው ተገልጿል። “Use or Freeze By 06-19-25” and “Use or Freeze By 06-20-25”

ይህ ምርት በከነቲከት፤ ጆርጂያ፤ ኤሊኖይና ሜሪላንድ ላሉ አከፋፋዮች የተላከ ሲሆን የተከፋፈለ ሲሆን በመላው ዩናይትድ ስቴትስ ባሉ የሆል ፉድስ መደብሮች ሲሸጥ እንደከረመ ታውቋል።

ይህ ምርት በአሁኑ ሰዓት በገበያ ላይ እንደሌለና ሁሉም ምርቶች ተሸጠው እንዳለቁ የተነገረ ሲሆን ሰዎችን በቤታቸው ያሉ ፍሪጆችና ፍሪዘሮች ውስጥ ይህ ምርት መኖር አለመኖሩን እንዲያረጋግጡና ካሉ በፍጹም ለምግብነት እንዳይውሉ መንግስት መክሯል። የመንግስት መግለጫ አክሎም ይህን ምርት የገዙ ሰዎች ወይ እንዲጥሉት አልያም የገዙበት ቦታ ወስደው ሪፈንድ እንዲጠይቁ መክሯል።
በኢኮላይ ጀርም የተያዘ ሰው ከሚያሳያቸው ምልክቶች ዋነኞቹ
- ተቅማጥና ከ102 ዲግሪ በላይ ትኩሳት
- ከ3 ቀን በላይ የሆነው ተቅማጥ
- ደም የተቀላቀለበት ተቅማጥ
- የማያባራ ትውከት
- የሰውነት መድረቅ (ውኃ ማጣት)
- ከባድ የሆድ ቁርጠት
እነዚህ ምልክቶች ባክቴርያው ወደሰውነት ከገባ ከ3-4 ቀናት ውስጥ ይከሰታሉ ተብሏል።