Screenshot 2022-12-09 at 16.24.24

ቶሪ ሙር የተባለው ይህ ወንጀለኛ ከዚህ ቀደም እጮኛውንና በማህጸኗ የነበረውን ጽንስ በአሰቃቂ ሁኔታ ከገደለ በኋላ ከፖሊስ ተስውሮ ቆይቶ ኋላ ላይ ደሞ ኒው ኃምፕሻየር አቬኑ ላይ ከሚገኝ ጋዝ ስቴሽን በመግባት የጋዝ ስቴሽን አገልጋይ የነበሩትን አቶ አያሌው ወንድሙን መነሻው ምን እንደሆነ ያልታወቀ ጸብን ተከትሎ በጥይት ተኩሶ እንደገደላቸው ዘግበን ነበር።

ቶእሪ ሙር ታዲያ ከሰሞኑ የፍርድ ቤት ቀጠሮ የነበረው ሲሆን በዚህ ቀጠሮው ዳኛው ሶስት የዕድሜ ይፍታህ እስር አከናንበውታል።

Image: Fox5

የ34 አመይ ወጣት የሆነው ቶሪ ሙር ባሳለፍነው አርብ በነበረው የፍርድ ቤት ውሎ በ2022 የ8 ወር እርጉዝ የነበረችውን የ26 አመት ወጣት እጮኛውን ዴኒስ ሚድልተንንና ያልተወለደ ልጃቸውን በመግደል ወንጀል ወንጀለኛ ተብሎ ተፈረደበት።
ቶሪ ሙር በሞንጎምሪ ካውንቲ ታሪክ የመጀመሪያው ያልተወለደ ጽንስን ነፍስ በማጥፋት ወንጀለኛ የተባለ ሰው ሆኗል።
ወንጀሉ በተፈጸመበት ወቅት የሙር እጮኛ የሆነችው ዴኒስ ሚድልተን የ8ወር ተኩል ነፍሰጡር የነበረች ሲሆን ፖሊሶች ተጠርጣአሪውን በሌላ ወንጀል ጠርጥረውት ለፍተሻ ቤቱ ሲሄዱ በመበስበስ ላይ የሚገኝ ሬሳ እንዳገኙ ከዚህ ቀደም በሰራነው ዘገባ አስነብበን ነበር።


ቶሪ ሙር ለዚህ ወንጀል ፍርዱን ለመቀበል ለማርች 28 2025 ቀጠሮ የተሰጠው ሲሆን ከዚህ ወንጀል በተጨማሪም በ2022 የጋዝ ስቴሽን ሰራተኛ የነበሩትን የ61 አመቱን አቶ አያሌው ወንድሙን ነፍስ በማጥፋት ወንጀል ፍርዱን እየተጠባበቀ ይገኝ የነበረ ሲሆን ባሳለፍነው ሳምንት ፍርዱን አግኝቷል።


ለጥቆማው ሉላን እናመሰግናለን።

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት

Sign In

Register

Reset Password

Please enter your username or email address, you will receive a link to create a new password via email.