ፌርፋክስ አፎርደብል

በቨርጂንያ ፌርፋክስ ካውንቲ የአፎርደብል ሃውሲንግ ቤቶች ለማግኘት የሚሹ ሰዎች ከትላንት ሰኞ ጁን 2 2025 ጀምሮ እስከ ዕሁድ ጁን 8 2025 ኦንላየን ሬንት-ካፌ ላይ በመግባት በተጠባባቂነት መመዝገብ እንደሚችሉ ተገልጿል፡፡ በዚህ የተጠባባቂ ምዝገባ ላይ በመመዝገብ በቀጣይ በነዚህ አፓርታማዎች በሚኖሩ ክፍት ቦታዎች ላይ ተመዝጋቢዎች በሎተሪ መልክ እድለኞች የቤት ባለቤት ይሆናሉ።
በአሁኑ የተጠባባቂዎች ምዝገባ እጣ የሚደርሳቸው ሰዎች በግል ድርጅቶች ስር ለሚገኝ መኖሪያ ቤቶችና መንግስት ራሱ በሚያስተዳድራቸው መኖሪያ ቤቶች ባሉ ክፍተቶች እንደሚገቡ ተነግሯል።
በዚህ ዙር ነዋሪዎችን የሚቀበሉ የመኖሪያ አፓርታማዎች ዝርዝርም የሚከተለው ነው።

  • Hollybrook III (one and two bed), 3012 Patrick Henry Drive, Falls Church, VA 22044,
  • Creekside Village (one, two and three bed), 7979 Janna Lee Avenue, Alexandria, VA 22306
  • The Arden (one, two and three bed), 2317 Huntington Avenue, Alexandria, VA 22303
  • One University – The Robinson (two bed), 4530 University Drive, Fairfax, VA
  • Madison Ridge (one and two bed), 14806 Rydell Road, Centerville, VA 20121
  • Ovation at Arrowbrook (one and two bed), 13325 Fairfield Ridge Avenue, Herndon

በነዚህ አፓርታማዎች ተጠቃሚ ለመሆን ነዋሪዎች ገቢያቸው ከተፈቀደው በላይ መሆን የለበትም። በፌርፋክስ ካውንቲ በዚህ እድል ለመጠቀም ለማነጻጸሪያነት የሚቀርበው የገቢ ደረጃ እንደሚከተለው ተቀምጧል።

ማንኛውም በዚህ መልካም ዕድል መጠቀም የሚፈልግ ሰው ይህን ሊንክ በመጫን በካውንቲው ድረገጽ በመግባት ማመልከት ይችላል።

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት

Sign In

Register

Reset Password

Please enter your username or email address, you will receive a link to create a new password via email.