@ethiopique202 (88)

የፌርፋክስ ካውንቲ ፖሊስ ከአንድ ሰዓት በፊት ባወጣው የአፋልጉኝ ማስታወቂያ ላይ እንደተቀመጠው የ52 አመት ጎልማሳ የሆኑትን ወይዘሮ አብረኸት ምራጭን አፋልጉኝ ያለ ሲሆን ተፈላጊዋ ለመጨረሻ ጊዜ የታዩት ትላንት አርብ ሜይ 30 ጧት 10፡34 አካባቢ በታይሰን 8300 Greensboro Drive አካባቢ እንደሆነ ተነግሯል።

ወይዘሮ አብረኸት ቁመታቸው 5 ጫማ ከ 4 ኢንች ሲሆን ክብደታቸው ደሞ 130 ፓውንድ ሲሆን ቡናማ የአይንና የጸጉር ቀለም አላቸው ተብሏል። ተፈላጊዋ ለመጨረሻ ጊዜ በታዩበት ወቅት ጥቁር ጃኬት በዥንጉርጉር ቀሚስና ዥንጉርጉር ሻርፕ ለብሰው እንደነበርም ተነግሯል።


ተፈላጊዋ ባለባቸው የአካል/የአዕምሮ ደህንነት ምክንያት በአደጋ ላይ ወድቀው ሊሆን እንደሚችል ፖሊስ ጠቁሟል።

የወይዘሮ አብረኸትን መገኛ የሚያውቅ ወይንም ከጠፉበት ጊዜ በኋላ አይቼያቸዋለሁ የሚል ሰው ለፖሊስ በስልክ ቁጥር 703-691-2131 ደዎሎ እንዲጠቁም ተጠይቋል።

መረጃውን ያደረሰንን አንተነህ ደመላሽን እናመሰግናለን።

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት

Sign In

Register

Reset Password

Please enter your username or email address, you will receive a link to create a new password via email.