@ethiopique202-1

የፍሎሪዳ የህዝብ ምክር ቤት ተወካይ የሆኑት የሪፐብሊካን ኮንግረስ አባል ግሬግ ስቱብ ዛሬ ሐሙስ ሜይ 29 ባቀረቡት ረቂቅ ህግ መሰረት የዲሲ የህዝብ ባስና ሰብዌይ ሲስተም የሚያስተዳድረው ተቋም በትራምፕና በንቅናቄያቸው ማጋ (MAGA) ስም እንዲሰየም ጠይቀዋል፡፡ 

ይህ ረቂቅ የሜክ አሜሪካ ግሬት አጌን አዋጅ ተብሎ የተሰየመ ሲሆን የዋሽንግተን ሜትሮፖሊታን ኤሪያ ትራንዚት ኦቶሪቲ (WMATA) ስሙ ተቀይሮ ዋሽንግተን ሜትሮፖሊታን ኦቶሪቲ ፎር ግሬተር አክሰስ (WMAGA) እንዲባል የጠየቁ ሲሆን ባቡሮቹም የትራምፕ ባቡር ተብለው እንዲጠሩ ከመጠየቅ ባለፈ ተቋሙ በዚህ የስም ቅያሬ ካልተስማማ ከፌደራል መንግስ የሚያገኘው በሚልየን ዶላሮች የሚቆጠረው የገንዘብ ድጎማ እንዲቋረጥበት ይደነግጋል፡፡ 

ከዚህ ቀደም እንደዘገብነው የኖርዝ ካሮላይና የህዝብ ተወካይ አዲሰን ማክዶወል የደለስ አየር ማረፊያን በትራምፕ ስም እንዲቀየር እንዲሁም የሳውዝ ካሮላይና ጆ ዊልሰን ደሞ የትራምፕ ፎቶ የያዘ አዲስ አዲስ የ250 ዶላር ቢል እንዲታተም ጠይቀው ነበር፡፡

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት

Sign In

Register

Reset Password

Please enter your username or email address, you will receive a link to create a new password via email.