@ethiopique202 (83)

ዘንድሮ መቶኛ አመቱን ባከበረው የብሄራዊው የስፔሊንግ ቢ የልጆች የስፔሊንግ ውድድር ፕፕሪንስ ጆርጅ -ናሽናል ሀርበር፤ ሜሪላንድ በሚገኘው ጌይሎርድ ሆቴል በተከናወነበት ወቅት ከ50ዎቹም ስቴቶች የተወከሉ 243 ታዳጊዎች ተወዳድረዋል።
ከነዚህም መሀል ታዲያ የኛዎቹ ሚካኤል ተስፋዬ ከቴክሳስ፤ አማኑኤል ገመቺስ ከ ሳውዝ ዳኮታና አይዛክ ገረመው ከፔንሳልቬንያ ይገኙበታል። ምንም እንኳ ሶስቱም በተለያየ ደረጃ ላይ ከውድድሩ ቢወጡም ለመጡበት ማህበረሰብና ለቤተሰቦቻቸው ግን ኩራት መሆናቸው አልቀረም።

ሚካኤል ተስፋዬ የ14 አመት ታዳጊና በክራይስት ዘ ኪንግ ትምህርት ቤት የ8ኛ ክፍል ተማሪ ሲሆን በባለፈው አመት ውድድር 177ኛ ሆኖ ጨርሶ ነበር። ከትምህርት በተጨማሪ ሚካኤል ባስኬትቦል፤ ፉትቦልና ቪዲዮ ጌም የሚያዝናናው ሲሆን የለብሮን ጄምስ አድናቂ እንደሆነም ተናግሯል።


አማኑኤል ገመቺስ ደግሞ ከሱው ፎልስ ሳውዝ ዳኮታሲሆን የመጣው የጆርጅ ኤስ ሚክልሰን መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪ ነው። አማኑኤል ጎበዝ የቫዮሊን ተጫዋችን አንባቢ ሲሆን የእግር ኳስ ጨዋታም እንደሚያዝናናው ተናግሯል። በትርፍ ጊዜው እንደ ፓሮት ካሉ ፓራኪት ከተባሉት የቤት ወፎቹጋ በመጫወት ጊዜውን እንደሚያሳልፍ ተናግሯል።

አይዛክ ገረመው ደሞ የ13 አመት ታዳጊና ፊላደልፊያ በሚገኘው የዊልያም ዴቪስ መካከለኛደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪ ሲሆን በ2023 ዓመተ ምህርረት በነበረው የስፔሊንግ ቢ ውድድር 23ኛ ደረጃን አግኝቶ ነበር።

በዘንድሮው ውድድር 74ኛ ደረጃን አግኝቶ አጠናቋል። አይዛክ በስነ ህዋ፤የሂሳብ ትምህርትና ቋንቋ ትምህርቶች ፍላጎት እንዳለውና በአሁኑ ሰዓትም የጀርመንኛና የፈረንሳይኛ ቋንቋዎችን እየተማረ እንደሆነ ተናግሯል። በምሽት ቴሌስኮፑን ወደ ሰማይ አርጎ ከዋክብትን መመልከት እንደሚያዝናናውና በትርፍ ጊዜው ደሞ መጽሀፍ እየጻፈ እንደሆነ ተናግሯል።

የስፔሊንግ ቢ የመጨረሻ ውድድር ነገ ናሽናል ሀርበር በሚገኘው የጌይሎርድ ሆቴል ይከናወናል። የኢትዮጲክ ባልደረቦች ለሚካኤል፤ አማኑኤልና አይዛክ እንዲሁም ለቤተሰቦቻቸው እንኳን ደስ ያላችሁ ይላሉ።

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት

Sign In

Register

Reset Password

Please enter your username or email address, you will receive a link to create a new password via email.