@ethiopique202 (80)

ማስጠንቀቂያው ሐሙስ ሜይ 29 ከሰዓት 2:30pm ጀምሮ ተነስቷል::

…..

የሪችመንድ ከተማ ባለስልጣናት ዛሬ ማክሰኞ ሜይ 27 ማለዳ ላይ የከተማዋ የውሃ ማጣሪያ ፋብሪካ ላይ የአሰራር ችግር ከገጠመው በኋላ ለበርካታ ሰፈሮች ውሃ አፍልቶ የመጠቀም ማስጠንቀቂያ ሰጥተዋል።

ችግሩ የተፈጠረው ከፍተኛ የሆነ የቆሻሻና ዝቃጭ ጥርቅም የውሃ ማጣሪያውን ፊልተር በመድፈኑ ነው ተብሏል። ይህም ጊዜያዊ የንፁህ ውሃ ምርት እንዲቀንስ እና እንደ ስኮትስ አዲሽን፣ ዘ ፋን፣ ሙዚየም ዲስትሪክት፣ ጃክሰን ዋርድ፣ ቸርች ሂል፣ እና ኖርዝሳይድ ባሉ አካባቢዎች የውሃ ግፊት እንዲቀንስ አድርጓል።

ይህ ክስተት በዚህ ዓመት በሪችመንድ ሁለተኛው ትልቅ የውሃ ስርዓት መቋረጥ ነው። በጃንዋሪ ወር፣ በተመሳሳይ የውኃ ማጣሪያው የመብራት ሀይል መቋረጥ ተከትሎ ወደ 230,000 የሚጠጉ ነዋሪዎችን ለአንድ ሳምንት ያህል ያለ አስተማማኝ የመጠጥ ውሃ አስቀርቶ ነበር።

በቨርጂኒያ የጤና ቢሮ ያወጣውው መግለጫ ታዲያ ያንን ቀውስ ማስቀረት ይቻል እንደነበርና ይህ ሊከሰት የቻለው የከተማው አስተዳደር በቂ ያልሆነ የአደጋ ጊዜ እቅድ ባለማዘጋጀቱ እና በቂጥገና ባለማድረጉ እንደሆነ አስታውቀዋል።

ከንቲባ ዳኒ አቩላ የአሁኑን ብልሽት በጥልቀት እንደሚያጣሩ እና የከተማዋን የውሃ መሠረተ ልማት አስተማማኝነት ለማረጋገጥ የረጅም ጊዜ የመከላከያ እርምጃዎች እንደሚያስፈልግ አጽንዖት ሰጥተዋል።

በነዚህ አካባቢዎች ያሉ ነዋሪዎች ምን ማድረግ ይጠበቅባቸዋል?

  • በቧንቧ ውኃ የተሰሩ በረዶዎችንና ሌሎች መጠጦችን ያስወግዱ
  • ውኃ ከቧንቧ ሲወርድ ቀለሙን ከቀየረ ንጹህ ውኃ መፍሰስ እስኪጀምር ቧንቧውን ከፍተው ይተዉት
  • የታወቁ የሊድ ምንጮች ካሉ ቀዝቃዛ ውኃ ለሁለት ደቂቃ ያፍሡ
  • ውኃውን ቢያንስ ለ1 ደቂቃ በደንብ ያፍሉትና አቀዝቅዘው ይጠቀሙ
  • የቀዘቀዘውን ውኃ በንጹህና በተሸፈነ ማስቀመጫ ያኑሩት

በዚህ ወቅት ፈልቶ የቀዘቀዘ ውሃ ወይም የታሸገ ውሃ ብቻ ለሚከተሉት አገልግሎቶች ጥቅም ላይ መዋል አለበት፡

  • ለመጠጥ
  • ጥርስ ለመቦረሽ
  • ምግብ ለማብሰል እና ማዘጋጀት
  • ፍራፍሬዎችን እና አትክልቶችን ለማጠብ
  • የሕፃናት ፎርሙላ ለማዘጋጀት
  • በረዶ ለመሥራት
  • ለቤት እንስሳት የመጠጥ ውሃ ለመስጠት

በፍጹም የውኃ ማጣሪያ ማሽኖችን ብቻ ተማምነው ውኃ ከማፍላት እንዳይዘናጉ።

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት

Sign In

Register

Reset Password

Please enter your username or email address, you will receive a link to create a new password via email.