@ethiopique202 (79)

የሜሪላንድ እና ዋሽንግተን ዲ.ሲ. ነዋሪዎች ከጁን 1, 2025 ጀምሮ የኤሌክትሪክ ክፍያ ጭማሪ ይገጥማቸዋል ተባለ። በአካባቢው ለብዙ ደንበኞች ኤሌክትሪክ የሚያቀርበው ፔፕኮ (Pepco) የተባለው ኩባንያ፣ አንድ መካከለኛ ቤተሰብ በወር ከ15 እስከ 18 ዶላር የሚደርስ ጭማሪ ሊያጋጥማቸው እንደሚችል አስታውቋል።

ይህ ለውጥ በኃይል ገበያው ውስጥ ባለው የዋጋ ጭማሪ ምክንያት ሲሆን ይህም ፔፕኮ ለቤቶች እና ለንግድ ድርጅቶች ኃይል ለማቅረብ የሚወጣውን ወጪ ስለሚጨምረው ነው ተብሏል።
በአማካይ በወር እስከ 1,000 ኪሎዋት-ሰዓት ኤሌክትሪክ ለሚጠቀም መደበኛ ቤት፣ በአዲሱ ዋጋ ከወትሮው ከፍ ያለ ክፍያ ያስከትላል። ወጪዎቹ የአቅርቦት ክፍያ፣ የማጓጓዣ ክፍያ፣ የማድረሻ ክፍያዎች እና ቋሚ የደንበኝነት ክፍያን ያካትታሉ። እነዚህ ሁሉ ክፍያዎች ተደምረው፣ በበጋ ወራት ደግሞ የአየር ማቀዝቀዣዎች በብዛት ጥቅም ላይ ሲውሉ፣ ክፍያዎቹ የበለጠ ከፍ እንዲሉ ያደርጋሉ።


ይህንን የኤሌክትሪክ አከፋፋዮችና አቅራቢዎችን ውሳኔ በመቃወም የሜሪላንድ የህዝብ አገልግሎት ኮሚሽን እና 80 የክልል የህግ አውጪዎች ለፌዴራል ኢነርጂ ቁጥጥር ኮሚሽን (Federal Energy Regulatory Commission) ቅሬታ አቅርበዋል። የሜሪላንድስ የኃይል ማከፋፈያ የሚያስተዳደረውንና PJM ኢንተርኮኔክሽን (PJM Interconnection) የተባለውን ኩባንያ፣ የዋጋ መናርን የሚያስከትሉ ፍትሃዊ ያልሆኑ አሰራሮችን እየተጠቀመ ነው በማለት ከሰውታል።

ይህንን ተከትሎም ክረምት እየቀረበ ሲመጣ፣ ሰዎች የኤሌክትሪክ ፍጆታቸውን ለመቀነስ የሚያስችሉ መንገዶችን እንዲፈልጉ እየተበረታቱ ነው። ኃይል ቆጣቢ መሳሪያዎችን መጠቀም፣ የማያስፈልጉ መብራቶችን ማጥፋት እና ስማርት ቴርሞስታቶችን በመጠቀም ወርሃዊ ክፍያዎችን ለመቀነስ ይረዳል።


እነዚህ ለውጦች ማለት ብዙ ቤተሰቦች ለዚህ ክረምት ከፍተኛ ወጪዎችን ማቀድ አለባቸው ማለት ነው። ምንም እንኳን በርካታ ሰዎች የኤሌክትሪክ ፍጆታቸውን ለመቆጣጠርና ለመቀነስ የተሎእያዩ እርምጃዎችን መውሰድ ቢችሉም፣ የዋጋ ጭማሪው በሜሪላንድ ውስጥ መኖሩና ቤተሰቦችን መንካቱ አይቀርም።

የመብራት ሂሳባቸውን መክፈል የከበዳቸው የሜሪላንድ ነዋሪዎች ይህን ሊንክ በመጫን እገዛ ማግኘት ይችላሉ።

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት

Sign In

Register

Reset Password

Please enter your username or email address, you will receive a link to create a new password via email.