
የሞንጎምሪ ካውንቲ ፖሊስ ዛሬ ዕሁድ ባወጣው የአፋልጉኝ ማስታወቂያ ላይ እንዳስታወቀው አብረኃም ደበላ የተባሉትን የ83 ዓመት አዛውንት አፋልጉኝ ብሏል።
አቶ አብርኃም ደበላ ቁመታቸው 5 ጫማ ከ7 ኢንች ሲሆን ክብደታቸው 170 ፓውንድ ነው ተብሏል። አቶ አብርኃም ቡናማ የአይን ቀለምና ወደ ራሰ በራነት እየሄደ ያለ ሽበት የወረረው ጸጉር አላቸው ተብሏል።
አቶ አብርኃም ለመጨረሻ ጊዜ የታዩት ቅዳሜ ጁን 7 2025 ከሰዓት 2፡30pm ገደማ ሲሆን የታዩበት ቦታም በቤተስዳ በ6800 block of Melody Ln. አቅራቢያ ነው ተብሏል።
በወቅቱ የለበሱት ልብስ ምን አይነት እንደነበር አልታውወቀም ሆኖም አቶ አብርኃም የታርጋ ቁጥሩ 3DH8429 የሆነ ሰማያዊ የ2015 ቮልቮ XC60 እያሽከረከሩ ሊሆን እንደሚችል ተነግሯል።
የአቶ አብርኃምን መገኛ የሚያውቅ ሰውም በስልክ ቁጥር 301-279-8000 በመደወል ጥቆማ እንዲሰጥ ተጠይቋል።