
የፕሬዘደንት ትራምፕን 79ኛ አመትና የአ=ዩናይትድ ስቴትስ ሚሊታሪን 250ኛ ክብረ በአል በማስመልከት የሚደረጉ መጠነ ሰፊ የጎዳና ላይ ወታደራዊ ትዕይንቶች መዘጋጀቱን ተከትሎ የፕሬዘደንት ትራምፕን አስተዳደር እንቃወማለን አገዛዛቸው ቀስ እያለ አምባገነናዊና ፊውዳላዊ ቅርጽ እየያዘ መሄዱን እንቃወማለን የሚሉ ሰዎች ነገ የተቃውሞ ሰልፍ በመላው ዩናይትድ ስቴትስ ጠርተዋል።
በዲሲና አካባቢው ብቻ ከ100 በላይ በሆኑ አካባቢዎች የተቃውሞ ሰልፎች የተጠሩ ሲሆን ይህም አስቀድመው ለመንግስት የወታደራዊ ትሪዒት ከተዘጉት መንገዶችጋ ተደማምሮ ከፍተኛ የትራፊክ መጨናነቅ ሊያስከት እንደሚችል ይገመታል። ፕሬዘደንት ትራምፕ ስለ ተቃዋሚዎቹ ተጠይቀው በሰጡት መልስ ተቃዋሚዎች ከፍተኛ አጸፋዊ እርምጃ እንደሚወሰድባቸው ተናግረዋል። ፕሬዘደንቱ አያይዘውም በፍጹም ንጉስ እንዳልሆኑና ይህን ትርዒት ለማዘጋጅት በርካታ. መሰናክሎች እንዳለፉ ተናግረዋል።
በርካታ የስደተኞች ደህንነት ያሳስበናል የሚሉ ተቋማት የኢሚግሬሽን ጉዳያቸው ያልተቋጨና በጥቅሉ የአሜሪካ ዜግነትን ያላገኙ ሰዎች በነዚህ የተቃውሞ ሰልፎች እንዳይሳተፉ መክረዋል።
በዚህ የተቃውሞ ሰልፍ ዙሪያ በርካቶች መግለጫ ያወጡ ሲሆን ከነዚህ አንዱ የሆኑት የሜሪላንድ ገቨርነር ዌስ ሙር በሺዎች የሚቆጠሩ ሜሪላንዳውያን በዚህ ሰሞን የተቃውሞ ሰልፍ ሊያደርጉ እንዳቀዱ እንደሚያውቁና ይህ በህገመንግስት የተቀመጠላቸው ሀሳብን በነጻነት የመግለጽና የመሰብሰብ መብት በመሆኑ እሳቸውም ይህን ህገመንገስት ለማክበር ቃለ መኃላ መግባታቸውን በማስታወቅ የተቃዋሚዎችን ደህንነት ለማስጠበቅና ህግን ለማስከበር ከሚመለከታቸው አካላትጋ እንደሚሰሩ አስታውቀዋል።
እነዚህ የተቃውሞ ሰልፎች በዲሲና አካባቢው በሚከተሉት ቦታዎች ሊደረጉ ታቅደዋል።
- Arlington: Innovation Elementary School, 2300 Key Blvd, Arlington, VA 22201
- Bethesda: 7272 Wisconsin Ave, Bethesda, MD 20814
- Bowie: 15210 Annapolis Rd, Bowie, MD 20715
- Chevy Chase: Connecticut Avenue & East-West Highway, Elm St Urban Park- Note: Event is at capacity
- Fair Lakes: Fair Lakes Circle & Fair Lakes Parkway, VA 22033
- Fairfax: VA 2230,
- Falls Church: West Jefferson Street & North Washington Street, VA 22046
- Fredericksburg: Corner of William and Blue and Gray, 1516 William St, VA 22401
- Gaithersburg: Montgomery Village Avenue & North Frederick Avenue, Gaithersburg, MD 20879
- Garrett Park, MD: Strathmore Avenue, Garrett Park
- Herndon-Reston: Reston, VA 20194,
- Leesburg: Leesburg, VA, 20176,
- Manassas: Manassas Community Center at Marsteller Park, VA 20110
- Prince George’s County: U.S. 1 & Regents Drive, College Park, MD 20742
- Rockville: MD-355 Rockville, MD 20850,
- Silver Spring: Colesville Road/Rt 29 Beltway Overpass, MD 20901
- Springfield: Intersection of Old Keene Mill Road and Rolling Road, Springfield, VA 22152 (Cardinal Forest Shopping Center) – Note: Event is at capacity
- Takoma Park: Takoma Park Library (temporary location), 7505 New Hampshire Ave, Suite 205
- Woodbridge: Lake Ridge Commuter Lot, 12745 Minnieville Rd, VA 22192
በመላው አገሪቱ ያሉ የተቃውሞ ሰልፎችን ለማየት ይህን ሊንክ ይጫኑ