@ethiopique202 (99)

በሜሪላንድ የሞንጎምሪ ካውንቲ ፖሊስ ከጌትስበርግ ዛሬ ጁን 14 ባወጣው የአፋልጉኝ ማስታወቂያ የሲልቨርስፕሪንግ ነዋሪ የሆነችውን የ41 አመቷን ሳሌም ክብረዓብን አፋልጉኝ ብሏል።
የፖሊስ ሪፖርት እንደሚያሳየው ሳሌም ዕድሜዋ 41 ዓመት ሲሆን ቁመቷ 5 ጫማ ከ7ኢንች ነው። ሳሌም 180 ፓውንድ ክብደት ሲኖራት የአይኗ ቀለም ቡናማ እንዲሁም የፀጉሯ ቀለም ጥቁር እንደሆነ ፖሊስ በማስታወቂያው አትቷል።

ሳሌም ለመጨረሻ ጊዜ የታየችው ማክሰኞ ጁን 10 2025 እንደሆነና በወቅቱ ባለ ቀይ፤ ጥቁርና ነጭ ቀለም ሹራብ አርጋ ነበር ተብሏል። የሳሌምን መገኛ የሚያውቅ ወይንም ያያት ሰው ለፖሊስ በ301-279-8000 ደውሎ ጥቆማ እንዲያደርግ ፖሊስ ጠይቋል።

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት

Sign In

Register

Reset Password

Please enter your username or email address, you will receive a link to create a new password via email.