@ethiopique202 - 2025-06-14T142811.826

በበሚኔሶታ ቻምፕሊን ከተማ ነዋሪ የነበሩት የዴሞክራት ፓርቲ አባላትና የግዛቱ የተወካዮች ምክር ቤት አባላት የሆኑት ተወካይ ሆፍማንና ተወካይ ሆርትማን የተባሉ ፖለቲከኞች በመኖሪያ ቤታቸው ውስጥ የፖሊስ ልብስ በለበሰ ሰው በጥይት ተተኩሶባቸው ሜሊሳ ሆርትማንና ባለቤታቸ ወዲያው ለህልፈት ተዳርገዋል።

መርማሪዎች እስካሁን በግልጽ መረጃውን እንዳላወጡትና የምርመራ ስራው እንዳልተጠናቀቀ የተነገረ ሲሆን በርካቶች ይህን የፖለቲካዊ ይዘት ያለው ወንጀል ተቃውመው መግለጫ ሰተዋል።

የሚኒሶታ ገቨርነር ቲም ዋልዝ ዛሬ ጠዋት በሰጡት መግለጫም ግድያው ድንገተኛ እንዳልሆነና ታስቦበብትና ታቅዶበት የተፈጸመ እንደሆነ አስታውቀዋል።

ለህልፈት የተዳረጉት ተወካይ ሜሊሳ ሆርትማን ባሳለፍነው ሳምንት በነበራቸው የተወካዮች ምክር ቤት ስብሰባ ወቅት ሰነድ አልባ ለሆኑ ስደተኞች በሚኔሶታኬር በኩል ይሰጥ የነበረውን የነጻ የጤና ኢንሹራንስ እንዲቀር ድምጻቸውን ከሰጡ በኋላ ከሌሎች የዴሞክራት ፓርቲ አባላት ባልደረቦቻቸው ወቀሳን ሲያስተናግዱ ን እበር። ተወካዩአ ይህ ህግ እንዲጸድቅ ድጋፋቸውን የሰጡ ብቸኛዋ ዴሞክራት ነበሩ።

ይህን ወንጀል ፈጽሟል ተብሎ በተጠርጣሪነት የተፈረጀው የ57 አመት እድሜ ያለው ሉተር ቦልተር ሲሆን በገቨርነር ቲም ዋልዝ በ2019 በወርክፎርስ ዴቨሎፕመንት ቦርድ ውስጥ ተሹሞ ሲያገለግል የቆየ ሰው እንደሆነ ታውቋል። ይህ ግለሰብ በመኪናው ውስጥ ጸረ ጽንስ ማስወረድ ወረቀቶችና የሌሎች ኢላማዎች ስም ዝርዝር ይዞ የነበረ ሲሆን ዛሬ በሚደረገው የኖ ኪንግስ ሰልፍ ላይ የሚያዙ የሚመስሉ በራሪ ወረቀቶችንም ይዞ ነበር።

ይህንን ተከትሎም የሞንጎምሪ ካውንቲ ኤክስኪውቲቭ ማርክ ኤልሪችና የካውንቲው ካውንስል በጋራ ባወጡት መግለጫ በዚህ ፖለቲካዊ ይዘት ባለው የግድያ ወንጀ እጅግ ማዘናቸውንና መደንገጣቸውን አስታውቀዋል።

አክለውም ለተጎጂዎቹ ቤተሰቦች የኃዘን መግለጫና መጽናናትን የተመኙ ሲሆን በህዝብ ተመርጠው ስልጣን ላይ እንዳሉ ሰዎች ደሞ ፖለቲካዊ ነውጥ በፍጹም ቦታ ሊሰጠው እንደማይገባ ይልቅስ ለጤነኛ የኃሳብ ክርክሮችና ሰላማዊ ተቃሞዎች በር ክፍት ሊሆን እንደሚገባ ተናግረዋል።

እንዲህ ያሉ ተግባራት ሰዎች በነጻነት የህዝብ አገልጋይ እንዳይሆኑ እንደሚያደርግና የአገሪቱን ዴሞክራሲያዊ ሂደት እንደሚያደናቅፍ ገልጸዋል። በዛሬው ቀንም ከሚኔሶታውያንጋር በአንድነት እንደሚቆሙና ሁሉም በየደረጃው ያሉ መሪዎች በየትኛውም ፓርቲ ይህን ተግባር በግልጽ እንዲያወግዙ ጠይቀዋል።

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት

Sign In

Register

Reset Password

Please enter your username or email address, you will receive a link to create a new password via email.