@ethiopique202-1

የሞንጎምሪ ካውንቲ ፖሊስ ባሳለፍነው ቅዳሜ በዳውንታውን ሲልቨር ስፕሪንግ በሚገኘው የኤሊስወርዝ ድራይቭ የመኪና ማቆሚያ ጋራጅ ላይ ዘሎ በመውደቅ ለህልፈት የተዳረገውን ሰው ማንነት ለመለየት መቸገሩንና የሚያውቁት ሰዎች ለፖሊስ ሪፖርት እንዲያደርጉ ጠይቋል፡፡ 

አደጋው የደረሰው ቅዳሜ ሜይ 10 2025 ምሽት 9፡57 ገደማ ሲሆን ሟች በላዩ ላይ ማንነቱን የሚገልጽ ምንም መታወቂያ አልተገኘበትም፡፡ ሟች ጥቁርና ዕድሜው ከ20᎒0 የሚገመት ሲሆን በወቅቱ ነጭ ረጅም እጅጌ ያለውና የናይኪ ሎጎ ያለው ሹራብና ግራጫ የመሮጫ ቱታና ግራቻ ጫማ አርጎ ነበር ተብሏል፡፡ 

Image: mcpnews

ፖሊስ ይህን ሰው የሚያውቀው በስልክ ቁጥር 301 279 8000 ደውሎ እንዲያሳውቅ ጠይቋል፡፡ 

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት

Sign In

Register

Reset Password

Please enter your username or email address, you will receive a link to create a new password via email.