@ethiopique202-1

ዋሽንግተን ዲሲ በመጪው ጁን ወር በሜትሮባስ ሲስተም ላይ ትልቅ ለውጥ ይደረጋል ተባለ። አዲሱ እቅድ “የተሻሻለ የአውቶቡስ ኔትወርክ” ተብሎ የሚጠራ ሲሆን የአውቶቡስ ጉዞ ለሁሉም ሰው ፈጣን እና አስተማማኝ እንዲሆን ታስቦ የተዘጋጀ ነው።

አንዱና ትልቁ ለውጥ በጣም ተቀራርበው ያሉ ወይም ብዙም ጥቅም ላይ የማይውሉ ከ500 በላይ የአውቶቡስ ማቆሚያዎችን ማስወገድ ነው። ይህ አውቶቡሶች በፍጥነት እንዲንቀሳቀሱ እና በጊዜ መርሃ ግብራቸው እንዲቆዩ ይረዳል። መንገደኞች ብዙ ሳይራመዱ በአቅራቢያ ያሉ ማቆሚያዎችን መጠቀም ይችላሉ።

አዲሱ እቅድ የአውቶቡስ መስመሮችን ለመሰየም አዲስ መንገድን ያካትታል። ለምሳሌ፣ በከተማው መሃል ወይም ዳውንታውን በኩል የሚያልፉ አውቶቡሶች በ”D” ፊደል የሚጀምሩ ሲሆን በከተማው ውስጥ አቋርጠው የሚጓዙ አውቶቡሶች ደግሞ በ”C” ይጀምራሉ። ይህ የትኛውን አውቶቡስ መውሰድ እንዳለቦት ለመረዳት ቀላል ያደርገዋል።

አውቶቡሶች ይበልጥ ፈጣን እንዲሆኑ ከተማዋ ቢያንስ 12 አዳዲስ ለአውቶቡሶች ብቻ የተሰሩ መስመሮችን እየጨመረች ነው። እነዚህ መስመሮች ለአውቶቡሶች ብቻ የተሰሩ ናቸው፣ ስለዚህ በመደበኛ ትራፊክ ውስጥ አይካተቱም። በአውቶቡሶች ላይ የተገጠሙ ካሜራዎች በእነዚህ መስመሮች የሚነዱ ወይም የሚያቆሙ መኪኖችን ለመያዝና ለመቅጣት ይረዳሉ፣ አሽከርካሪዎች አውቶቡስ መንገድ ላይ ካቆሙ ወይም ሲነዱ ከተገ ቅጣት ሊጣልባቸው ይችላል።

የከተማ ባለስልጣናት አዲስ የባቡር መስመሮችን ከመገንባት ይልቅ አውቶቡሶችን ለማሻሻል እየመረጡ ያሉት አዳዲስ የባቡር መስመሮች ብዙ ገንዘብ የሚጠይቁ እና ለመገንባት ረጅም ጊዜ የሚወስዱ በመሆናቸው ነው ብለዋል። አውቶቡሶች ርካሽ ናቸው፣ ለማሻሻል ፈጣን ናቸው፣ እና ብዙ ሰፈሮችን መድረስ ይችላሉ።

“የተሻሻለው የአውቶቡስ ኔትወርክ” ጁን 29 ይጀምራል። ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ወይም የአውቶቡስ ጉዞዎን ለማቀድ በ wmata.com/BetterBus ላይ መጎብኘት ይችላሉ።

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት

Sign In

Register

Reset Password

Please enter your username or email address, you will receive a link to create a new password via email.