@ethiopique202 (52)

ኤፕሪል 30 ንጋት 1am አካባቢ ቨርጂንያ በ5800 ቤይሊስ ክሮስ ሮድ ሰፈር ብላክ ሮዝ ላውንጅ አቅራቢያ በተፈጠረ አለመግባባት አንድ ሰው ተተኩሶበት ወደ ሆስፒታል ተወስዷል። የጥይት ሰለባ የሆነው ሰው ከጉዳቱ እያገገመ እንደሆነም ፖሊስ አስታውቋል።


እንደፖሊስ ሪፖርት ከሆነ በሁለት ሰዎች መሀል አለመግባባቱ ከተከሰተ በኋላ ተጠርጣሪው ሽጉጥ በማውጣት ተጎጂውን በበርካታ ጥይት አቁስሎታል።


ፖሊስ በቦታው የነበሩ እማኞችን እንዳነጋገረና ተኳሹ ግን አስቀድሞ ስላመለጠ ሊይዘው እንዳልቻለም አስታውቀዋል።

በዚህ ጉዳይ መረጃ ያለው ማንኛውም ሰው ለፌርፋክስ ካውንቲ ፖሊስ በስልክ 703-867-2222 አልያም ለፌርፋክስ ክራይም ሶልቨርስ በ1-866-411-TIPS በመደወል ጥቆማ እንዲሰጥ ፖሊስ ጠይቋል።

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት

Sign In

Register

Reset Password

Please enter your username or email address, you will receive a link to create a new password via email.