Petworth Porchfest

Image: Gemini

በ2021 በፓንደሚኩ ወቅት ሰዎች በቤታቸው ታሽገው በነበረበት ወቅት የጉርብትና መንፈስ እንዳይጠፋ ብለው የጀመሩትና አሁን የዲሲ ባህል ሆኖ የቀረው ፖርች ፌስት ትላንትናና ዛሬ ይከናወናል።

ትላንት በ801 Taylor St NW በነበረው ፕሮግራም በዋናው መድረክ ላይ ሶስት ባንዶች የሙዚቃ ስራዎቻቸውን ያቀረቡ ሲሆን ዛሬ ደሞ በፔትወርዝ በተሰባጠሩ ከ60 በላይ በሆኑ የመኖሪያ ቤቶች በረንዳዎች ላይ ከ100 በላይ ባንዶችና አርቲስቶች ከ 2pm እስከ 6pm ባለው ጊዜ ፕሮግራማቸውን ያቀርባሉ።

ይህ ፕሮግራም ለማንኛውም ሰው በነጻ የሚገባበት ሲሆን ተመልካቾች ከበረንዳ ወደ በረንዳ እየተዘዋወሩ መጎብኘት ይችላሉ።

የፕሮግራሞቹን መገኛ እንዲሁም የምግብ ቤቶችና መጸዳጃ ቤቶች መገኛ ካርታ ለማየት ይህን ይጫኑ።

የፖርች ፌስት ፕሮግራም

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት

Sign In

Register

Reset Password

Please enter your username or email address, you will receive a link to create a new password via email.