@ethiopique202 (47)

በሮበርት ኤፍ ኬኔዲ የሚመራው የፌደራል መድኃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን መስሪያ ቤት ዛሬ ባወጣው መግለጫ እንዳሳወቀው ከፔትሮሊየም የሚሰሩ የምግብ ማቅለሚያዎችን ሙሉ ለሙሉ በ2026 እንደሚያግድ አስታውቋል። ይህ እርምጃ ሮበርት ኤፍ ኬኒዲ ሜክ አሜሪካ ሄልዚ አጌን ብለው ባወጁት እቅድ ላይ ተመስርቶ በተለይም ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን ለመከላከል ባለመው እቅዳቸው መሰረት የሚተገበር እቅድ ነው ተብሏል።

የዚህ እቅድ የመጀምሪያው አላማ የተባለውም ከምግብ ውስጥ ጤናማ ያልሆኑ ኬሚካሎችንና ንጥረነገሮችን ማስወገድ አንዱ ነው ተብሏል።

በመግለጫው እንደተነገረው በጤና ላይ ዕክል እንደሚያመጡ በሳይንስ ማስረጃ የተገኘባቸው ኬሚካሎች በሌላ አገራት ሲከለከሉ እስካሁን በአሜሪካ አገልግሎት ላይ ሲውሉ ይገኛሉ።


የፌደራል መድኃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን ኮሚሽነር የሆኑት ዶክተር ማርቲ ማካሪ እንዳሉትም ለምግብ ማቅለሚያ የሚሆኑ ደህንነታቸው የተጠበቁ እንደ ቀይስር፤ ካሮትና ሀብሀብ የመሳሰሉ ተፈጥሯዊ ማቅለሚያዎችን መጠቀም እንደሚቻል ተናግረዋል።

ባለሙያው አክለውም ላለፉት አስርት አመታት በአገራችን ባሉ ህጻናት ላይ ተገቢ ያልሆነ ምርምር ስናደርግ ቆይተናል፤ ይህ ግን አሁን ይቆማል። የአሜሪካ ህጻናት የተሻለ ጤናማ ስርዓት ይሻሉ ብለዋል።


ይህ ውሳኔ ጃንዋሪ 15 በኤፍ ዲ ኤ የተከለከለውን ቀይ የምግብ ማቅለሚያ ኬሚካልን ተከትሎ የተወሰነ ውሳኔ ነው ተብሏል።

📌 ከዚህ ቀደም የሰራነውን ዘገባ ይህን ተከትለው ያንብቡ: ቀይ የምግብ ማቅለሚያ ተከለከለ

የአሜሪካ ፌደራል የምግብና መድኃኒት ባለስልጣን ዛሬ እንዳሳወቀው ሬድ3 ተብሎ የሚጠራውን የምግብ ማቅለሚያ ለካንሰር ስለሚያጋልጥ ጥቅም ላይ እንዳይውል ከዛሬ ጃንዋሪ 15 ጀምሮ አግዷል፡፡

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት

Sign In

Register

Reset Password

Please enter your username or email address, you will receive a link to create a new password via email.