@ethiopique202 (27)

ከፌደራል መንግስት በኮቪድ ምክንያት ለስቴት ትምህርት ቤቶች የተሰጠውንና እስካሁን ወጪ ያልተደረገ ገንዘብ ወደካዝና ይመለሳል ተባለ።

ማርች 28 በፌደራል የትምህርት ዲፓርትመንት ዋና ሀላፊ በሆኑት ሊንዳ ማክማሆን ተፈርሞ የወጣው ደብዳቤ እንደሚያሳየው ከሆነ ስቴቶች በኮቪድ ወቅት ለመማር ማስተማር ሂደት ማገዣ እንዲሆን ተብሎ የተላከላቸውን ገንዘብ በ120 ቀናት ጥቅም ላይ እንዲያውሉ ቢያዝም እስካሁን ገንዘቡን ያልተጠቀሙበት ስቴቶች እንዳሉና የቀነ ገደቡ በማለፉ ከአርብ ማርች 28 2025 5pm ጀምሮ ይህንን ገንዘብ ወደ መንግስት ካዝና እንዲመለስ መወሰኑን አስታውቀዋል።


ቅሬታ ያላቸውና አጥጋሚ ምክንያት ያላቸው ስቴቶች ደሞ ይግባኝ በመጠየቅ ጉዳያቸው አንድ በአንድ እንደሚታይ በደብዳቤው ተጠቅሷል።

በርካታ ትምህርት ቤቶች ይህን ወደ 130 ቢልየን ዶላር የሚጠጋ ገንዘብ የመጨረሻ ዙር ክፍያ በመስከረም 2024 ፕላናቸውን አቅርበው በጃንዋሪ 2025 አጠናቀው መጠቀም ነበረባቸውም ተብሏል። ሆኖም በርካቶች ይህን ሳያደርጉ በመቅረታቸው ገንዘቡ ወደ ፌደራል መንግስት ተመላሽ ሆኗል።


ከነዚህም አንዱ የሜሪላንድ ትምህርት ቢሮ ነው። የሜሪላንድ ትምህርት ቢሮ የበላይ አስተዳዳሪ ኬሪ ራይት ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ የፌደራል መንግስቱ ከዚህ ቀደም የፈቀደላቸውንና 360 ሚልየን ዶላር መከልከላቸው እጅግ አስደንጋጭ እንደሆነና በየደረጃው ያሉ የትምህርት ተቋማትን እንደሚጎዳ ተናግረዋል።

ገንዘቡን በወቅቱ ማውጣት ያልተቻለውም በየጊዜው በተከሰተው የአቅርቦት እጥረት ምክንያት እንደሆነ ተናግረዋል። በዚህ ውሳኔ እጅጉን የሚጎዱትም የፕሪንስ ጆርጅ፤ የሞንጎምሪ ካውንቲና የባልቲሞር ከተማ የትምህርት ተቋማት ናቸው ተብሏል።

ይህንን ውሳኔ ተከትሎም በዚህ የገንዘብ ምንጭ ተግባራዊ የነበሩ አገልግሎቶችና ግንባታዎች እንዲቆሙ ተወስኗል።

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት

Sign In

Register

Reset Password

Please enter your username or email address, you will receive a link to create a new password via email.