@ethiopique202 (25)

በአሌክሳንድርያ ከተማ በርካታ ተማሪዎች ባሉባቸው አራት ኮሪደሮች ላይ አምስት የፍጥነት መቆጣጠርያ ካሜራዎችን ከኤፕሪል 2025 ጀምሮ በመትከል የማስጠንቀቂያ ትኬቶችን መላክ እንደሚጀምር የከተማው አስተዳደር አስታውቋል።
በዚህ ዙር ካሜራ ይገጠምላቸዋል የተባሉት መንገዶችም የሚከተሉት ናቸው።

  • የአሌክሳንድርያ ከተማ ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት – ኪንግ ስትሪት ካምፓስ (በኩዌከር ሌን እና በስክሮጊንግስ ሮድ መሀከል)
  • የአሌክሳንድርያ ከተማ ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት – ሚኒ ኃዋርድ ካምፓስ (ብራደክ ሮድ፣ በማርሊ ዌይ እና በማርቦሎሮ ድራይቭ መኃከል)
  • ዊልያም ራምሴ ኤለመንታሪ ስኩል – ኖርዝ ቢርጋርድ ስትሪት (በኖርዝ ሞርጋን ስትሪት እና ሮዋኖክ አቬኑ)
  • ሳውዝ ፒኬት ስትሪት – ከዱክ ስትሪት ወደ ኤድሳል ሮድ
  • አይዘንኃወር አቬኑ – ከሳውዝ ቫን ዶርን ስትሪት ወደ ቴሌግራፍ ሮድ

ከላይ የተጠቀሱት መንገዶች የተመረጡበት ምክንያትም ከዚህ ቀደም የነበሩ የመኪና ግጭቶች፤ የመኪና ትራፊክ መጨናነቅ፤ የመኪኖች ፍጥነት እንዲሁም የተማሪዎች እድሜና ቁጥር ከግምት ከግምት በማስገባት እንደሆነ ተነግሯል።

እያንዳንዱ የተጠቀሰው የትምህርት ዞን (ስኩል ዞን) ርዝማኔው ሩብ ማይል ያህል ሲሆን የትምህርት መውጫና መግቢያ ሰዓት ላይ የመኪኖች ፍጥነት ወሰን በሰዓት 15 ማይል ብቻ ነው።

አዲስ የሚገጠሙት የፍጥነት መቆጣጠሪያ ካሜራዎችም በዋናነት በነዚህ የትምህርት መውጫና መግቢያ ሰዓታት ላይ ይሆናል የሚሰሩት። ካሜራዎቹ በሚገጠሙባቸው ቦታዎች ላይም በግልጽ የሚቀመጡ ማስጠንቀቂያዎች ለአሽከርካሪዎች ይቀመጣሉ።

ከካሜራዎች በተጨማሪም በሳውዝ ፒኬት ስትሪት – ከዱክ ስትሪት ወደ ኤድሳል ሮድ እና በአይዘንኃወር አቬኑ – ከሳውዝ ቫን ዶርን ስትሪት ወደ ቴሌግራፍ ሮድ ከዚህ ቀደም ከነበራቸው የ35 ማይል በሰዓት የፍጥነት ወሰን ወደ 25 ማይል በሰዓት እንዲቀንሱ ይደረጋል ተብሏል።

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት

Sign In

Register

Reset Password

Please enter your username or email address, you will receive a link to create a new password via email.