
ፕሬዘደንት ትራምፕ ከተለያዩ የአለም አገራት በሚገቡ የመኪና ምርቶች ላይ የ25% ቀረጥ መጣላቸውን አስታውቀዋል፡፡ ይህ ታሪፍ ከኤፕሪል 2 ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ ሲሆን ከኤፕሪል 3 ጀምሮም ቀረጡ መሰብሰብ እንደሚጀምር ተነግሯል፡፡
ፕሬዘደንቱ ይህ ታሪፍ በአሜሪካ የመኪና ምርቶች እንዲበለጽጉና ተጨማሪ የስራ ዕድል እንዲፈጠር እንደሚያግዝ ተናግረዋል፡፡
በነበራቸው የጋዜጣ መግለጫ ላይ ይህ ታሪፍ ጊዜያዊ ይሁን አይሁን ተጠይቀው በሰስጡት ምላሽ ታሪፉ ቋሚ እንደሆነና አምራቾች መኪናቸውን በአሜሪካ ካመረቱ ግን ይህ ታሪፍ እንደማይመለከታቸው ተናግረዋል፡፡
ወደአሜሪካ ከሚገቡ መኪኖች አብዛኞቹ ከሜክሲኮ የሚገቡ ሲሆን በተጨማሪም ከደቡብ ኮርያ፤ ጃፓን፤ ካናዳና ጀርመን መኪንች ወደ አሜሪካ ይገባሉ፡፡
ይህን ተከትሎም የተለያዩ አገራት የአጸፋ እርምጃ ሊወስዱ ይችላል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ይህን ታሪፍ ተከትሎም የቶዮታና የሆንዳ ምርቶች በተለይም ዋጋቸው ሊያሻቅብ እንደሚችል ይገመታል፡፡