@ethiopique202-1

ዌይሞ የተባለው የሰው አልባ መኪኖች አምራች በዋሽንግተን ዲሲ የታክሲ አገልግሎት ለመስጠት ፍቃድ እንዲሰጠው ለዲሲ ጥያቄ አቅርቧል::

በድረ ገፁ ዛሬ እንዳሳወቀውም በ2026 በዋሽንግተን ዲሲ አገልግሎቱን ለመጀመር ዝግጅቱን እንደጨረሰና በቀጣይ ወራት አገልግሎቱን ለከተማው ነዋሪና ለአደጋ ተከላካይ ሰራተኞች ማስተዋወቅ እንደሚጀምር አስታውቋል::

ኡበር ስራ በጀመረባቸው የመጀመሪያ ወቅት በርካታ የዲሲ ታክሲዎች ገቢ መቀዛቀዙን ተከትሎ በኦክቶበር 2014 ታክሲ አሽከርካሪዎች ፔንስልቬኒያ አቬኑ ላይ መኪናቸውን በማቆም ተቃውመው ነበር::

አሁን ደሞ ዘመን ተቀይሮ ሰው አልባና ራሱን የሚሾፍር ታክሲ መምጣቱ ለበርካታ የታክሲ/ትራንስፖርት/ራይድ ሼር አገልግሎት ሰጪዎች ራስ ምታት ሊሆን ይችላል ተብሎ ይገመታል::

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት

Sign In

Register

Reset Password

Please enter your username or email address, you will receive a link to create a new password via email.