
በዲሲ ዩኒየን ስቴሽን አምትራክ ተሳፋሪ የነበረ ሰው በኩፍኝ እንደተያዘና በማርች 19 ወደ ደቡብ የሚሄድ የመስመር ቁጥር 175 ባቡር ምሽት 7:30pm እስከ 1:30am ተሳፋሪ እንደነበር ተነግሯል:: በመቀጠልም ማርች 22 11:00pm በ 1805 Columbia Rd NW በሚገኘው የሜድ ስታር ድንገትኛ ክፍል ህክምና አድርጏል::
የዲሲ መንግስት ሌሎች በዚህ በሽታ ወይም ምልክቱ ያለባቸው ሰዎች በአፋጣኝ ወደሀኪም እንዲሄዱ መክሯል::
ተጨማሪ መረጃ ስለኩፍኝ በሽታ ከዋሽንግተን ጤና ቢሮ
የኩፍኝ በሽታ
የኩፍኝ በሽታ በጣም ተላላፊ የሆነ በሽታ ነው። በተለይም ለትንንሽ ልጆች፣ ከባድ እና እንዲያውም ገዳይ ሊሆን ይችላል። የኩፍኝ በሽታን ለመከላከል ደህንነቱ የተጠበቀ እና በጣም ውጤታማ የሆነ ክትባት አለ። የኩፍኝ ክትባት እድሜው 1 አመት እና ከዚያ በላይ ለሆነ እያንዳንዱ ሰው ይመከራል። በዋሽንግተን ግዛት በትምህርት ቤት እና የልጅ እንክብካቤ ማዕከል ለመሳተፍ የኩፍኝ በሽታ ክትባት ያስፈልጋል። እንዲሁም በልጅ እንክብካቤ ማዕከል ወይም ቅድመ ትምህርት ቤት ውስጥ ለሚሰሩ ሰራተኞች እና በጎ ፈቃደኞች ያስፈልጋል። በዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ፣ “Measles, Mumps and Rubella (MMR፣ ኩፍኝ፣ ጆሮ ደግፍ እና የጀርመን ኩፍኝ)” እና “Measles, Mumps, Rubella and Varicella (MMRV፣ ኩፍኝ፣ ጆሮ ደግፍ፣ የጀርመን ኩፍኝ እና ቫሪሴላ)” የሚባሉ የኩፍኝ በሽታ ክትባቶች ይገኛሉ።
የኩፍኝ በሽታ ቫይረስ መረጃ
- የኩፍኝ ቫይረስ በአየር ውስጥ ይጓዛል። ቫይረሱ የኩፍኝ በሽታ ያለበት ሰው በነበረበት ክፍል አየር ውስጥ እስከ ሁለት ሰአታት ድረስ ስለሚቆይ ቫይረሱ ያለበት ሰው አቅራቢያ ከሄዱ ኩፍኝ ሊይዝዎት ይችላል።
- በሽፍታ ከመያዛቸው ቀደም ብሎ ከ4 ቀናት በፊት እና ሽፍታው ከታየ በኋላ እስከ 4 ቀናት ድረስ በበሽታው ከተያዘ ሰው የኩፍኝ በሽታ ሊይዝዎት ይችላል።
- በሽታ የመከላከል አቅም የሌለው እያንዳንዱ ሰው ለኩፍኝ ቫይረስ ከተጋለጠ በኩፍኝ በሽታ ይያዛል።
- የውጪ ሃገር ጉዞ ወይም ለውጪ ሃገር ተጓዦች መጋለጥ የኩፍኝ በሽታ ተጋላጭነትን ይጨምራል።
የኩፍኝ በሽታ፣ እንዲሁም የጀርመን ኩፍኝ የሚባለው፣ ከሁሉም የልጅነት የሽፍታ/ትኩሳት በሽታዎች በይበልጥ ገዳይ ነው። በአለም አቀፍ ደረጃ የልጆች ሞት ቀዳሚ መንስኤ ነው። የ U.S. Centers for Disease Control and Prevention (የአሜሪካ የበሽታ መቆጣጠሪያ እና መከላከያ ማዕከል) ስለ አገር አቀፍ የኩፍኝ በሽታ ወረርሺኝ (በእንግሊዘኛ እና በስፓኒሽ ብቻ) መረጃ አለው።
የኩፍኝ በሽታን ለመከላከል የተሻለው መከላከያ ክትባት መውሰድ ነው። የኩፍኝ ክትባቱ ደህንነቱ የተጠበቀ እና በጣም ውጤታማ ነው። እራስዎን እና ልጆችዎን በኩፍኝ፣ ጆሮ ደግፍ፣ እና የጀርመን ኩፍኝ (MMR) ክትባት (ሊንኩ በእንግሊዘኛ እና በስፓኒሽ ብቻ) መከላከልዎን ያረጋግጡ።
የኩፍኝ በሽታ ምልክቶች
የኩፍኝ በሽታ የሚጀምረው በ፦
- ትኩሳት
- ተቅማጥ
- ሳል
- የአፍንጫ ፈሳሽ
- ቀይ እና በእንባ የተሞሉ ዓይኖች
- የድካም ስሜት
ከጥቂት ቀናት በኋላ፣ ሽፍታ ይጀምራል፣ ይህም አብዛኛውን ጊዜ ፊት ላይ ጀምሮ በሙሉ ሰውነት ላይ ሊሰራጭ ይችላል።
በአንዳንድ ሰዎች፣ በተለይም ስር የሰደደ የህክምና ችግር ያለባቸው፣ ነብሰጡር የሆኑ፣ ወይም የተመጣጠነ ምግብ እጦት ባለባቸው ሰዎች ላይ፣ የኩፍኝ በሽታ እንደ የሳምባ ምች፣ የአንጎል ጉዳት፣ ዓይነ ስውርነት፣ መስማት መሳን፣ እና ሞት የመሳሰሉ ከባድ ችግሮችን ያስከትላል።
የኩፍኝ በሽታ አብዛኛውን ጊዜ ከ 7 እስከ 10 ቀናት ይቆያል።