ባሳለፍነው አርብ ጃንዋሪ 6 በኒውፖርት ኒውስ ቨርጂንያ በሚገኝ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት የአንደኛ ክፍል የሚማር የ6 አመት ህፃን ትምህርት ቤት ሽጉጥ ይዞ በመግባት አስተማሪውን በጥይት መቶ አቆሰለ። የኒውፖርት ኒውስ ከንቲባ ፊሊፕ ጆንስ ለጋዜጠኞች እንዳስረዱት አስተማሪዋ በ30ዎቹ እድሜ እንደሚገኙና በሆስፒታል እርዳታ እየተደረገላቸው ከጉዳታቸው እያገገሙ እንደሚገኙ አስረድተዋል።
የከተማው ባለስልጣናት ተኩሱ ድንገተኛ ሳይሆን ሆን ተብሎ የተደረግ እንደሆነና ህጻኑ አስተማሪዋ ላይ ከመተኮሱ በፊት ከአስተማሪው ጋር ተጣልተው ነበር ተብሏል። በቨርጂንያ ህግ መሰረት የ6 አመት ልጅ እንደ አዋቂ ስለማይቆጠር በፍርድ ቤት ሊከሰስ አይችልም። የታዳጊዎች ማረሚያ ቤት ለመግባትም እድሜው በጣም ልጅ በመሆኑ ፍርድ ቤት ልጁን ወደማረሚያ የመላክ ስልጣን የለወም ተብሏል። ፖሊስ ህጻኑ መሳሪያውን ከየት እንዳገኘና ሌሎች ስለተኩሱ ተጨማሪ መረጃዎችን ከመስጠት ተቆጥቧል።