ዋሽንግተን ዲሲ በብቸኞች ብዛት በአሜሪካ ካሉ ከተሞች ሁሉ አንደኛ ሆናለች። ይህ አዲስ ጥናት የአሜሪካንን የህዝብና ቤት ቆጠራ ተንተርሶ የተሰራ ሲሆን በአገር አቀፍ ደረጃ 29% ያህሉ የአሜሪካ ነዋሪ ብቻውን ነው የሚኖረው። በ2022 የወንዶች ትዳር መያዥ አማካይ እድሜ 301 ሲሆን ለሴቶች ደሞ 28.2 ነው ተብሏል።
ይህ ጥናት ይፋ እንዳደረገው ዲሲ በጠቅላላው 319,565 መኖሪያዎች ያሏት ሲሆን ነነዚህ ውስጥ ታዲያ 48.2 ከመቶው ወይንም 154፣140ው ብቻቸውን ነው የሚኖሩት። ጥናቱ በዲሲ ከ2016 ጀምሮ የብቸኞች ቁጥር በየአመቱ በ5.9% እያደገ ነው ብሏል።
በሁለተኛ ደረጃ የተቀመጠቸው ሴይንት ሉዊስ ሞንታና ስትሆን 66,357 ነዋሪዎቿ ወይንም 47.5% ነዋሪዎቿ ብቸኞች ናቸው ተብሏል። በሶስተኛ ደረጃ ላይ ደሞ ያለችው አሌክሳንድሪያ ቨርጂንያ ስትሆን ከተማዋ 33፣508 ነዋሪዎቿ ብቻቸውን የሚኖሩ ሲሆን ከጠቅላላው የከተማ ነዋሪ 46.5% ይሆናሉ።