በዲሲ ኖርዚስት ነዋሪ የሆነ ግለሰብ በመኖሪያ ቤቱ አካባቢ ያሉ መኪኖችን ለመስረቅ ሲሞክር ደርሼበታለሁ ያለውን የ13 አመት ታዳጊ በጥይት መቶ ለህልፈት ዳርጎታል። ፖሊስ ድርጊቱ የተፈጸመው አርብ ለቅዳሜ ለሊት ንጋት 4 ሰዓት ገደም በ1000 ብሎክ ኩዊንሲ ስትሪት አካባቢ ነው ያለ ሲሆን ፖሊስ የስልክ ጥሪ ደርሶት ወደቦታው ሲደርስ ታዳጊው በጥይት ተመቶ እያጣጣረ የነበረ ሲሆን የድንገተኛ አደጋ ሰራተኞች ህየውቱን ለማትረፍ ወደሆስፒታል ቢወስዱትም ታዳጊው ሆስፒታል ውስጥህይወቱ አልፏል። እንደፖሊስ መግለጫ ታዳጊው ካሮን ብሌክ የተባለ የዛው አካባቢ ኗሪና የብሩክላንድ ሚድልስኩል ተማሪ ነው።
ፖሊስ በተጨማሪም በአካባቢው የተሰረቀ መኪና እንዳገኘና ይኸው ታዳጊ ያሽከረክረው እንደነበር ገልጿል።