ማክሰኞ፣ ጥር 11፣ 2022
መላው የሞንትጎመሪ ህዝብ ለሞንትጎመሪ ሴቶች እና የሞንትጎመሪ ካውንቲ ለሴቶች የ2022 የሴት ታሪክ ሰሪዎች ሽልማት ኮሚቴ በሚያዘጋጀው የእውቅና ፕሮግራም ላይ ሴት እጩዎችን የእንዲሰይሙ ተጋብዘዋል ። የእጩዎች የማስመዝገቢያ የመጨረሻ ቀን ጃንዋሪ 20፣ በ11፡59 ፒኤም ነው።
ይህ ሽልማት በሞንትጎመሪ ካውንቲ ውስጥ ለሙያቸው እና በማህበረሰባችን ውስጥ ጉልህ አስተዋፅኦ ላደረጉ ሴቶች እውቅና ለመስጠት ነው። ብቁ ለመሆን፣ ተሿሚዎች ከሚከተሉት ውስጥ አንዱን ወይም ከዛ በላይ በምሳሌነት ማሳየት አለባቸው፡-
- ከራስ ወዳድነት ነፃ የሆነ አመራር እና በተሰማሩበት ዘርፍ ጠንክሮ መሥራት
- በሲቪክ እንቅስቃሴዎች ውስጥ ልዩ አመራር ማስመዝገብ
- አወንታዊ ማህበራዊ እርምጃ የሚያስከትሉ ፕሮግራሞችን ማዘጋጀት ወይም መደገፍ
- ለሌሎች መነሳሳት በአርአያነት ያገለገሉ
እጩዋ በሞንትጎመሪ ካውንቲ ውስጥ ነዋሪ ወይም ተቀጣሪ መሆን አለባት። የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሲኒየር ተማሪዎችና እና የኮሌጅ ተማሪዎችም ለሽልማቱ ሊታጩ ይችላሉ።
ይህንን ሊንክ በመጫንሊንክ በመጫን የመጠቆሚያውን ቅጽ መሙላት ይችላሉ። የእጩነት ቅጹ ሙሉ በሙሉ መሞላት አለበት። የሴቶች ታሪክ ሰሪ ሽልማት ተሸላሚዎች በመጋቢት ወር በሴቶች ታሪክ ወር እና በድጋሚ በፓናል ውይይት ተለይተው ይታወቃሉ። (ዝርዝሮች ወደፊት ይገለፅሉ)
ለበለጠ መረጃ ፡ Ijeoma.enendu@montgomerycountymd.gov ያነጋግሩ