ምስል፡ ከፌርፋክስ ላይብረሪ ገጽ
የ2023 የቨርጂንያ የህብ ቤተ-መጻህፍት ውድድር በተለያዩ ዘፎች የተከናወነ ሲሆን ከዘርፎቹ አንዱ በሆነው የፐብሊክ ላይብረሪ ኢኖቬተር አዋርድ ዘርፍ የህዝብ ቤተ-መጻህፍትን በቴክኖሎጂ ፈጠራ በማዘመን ዘርፍ አጥናፍ አምኃና ጌሪ ጉድሰን በጋራ አሸናፊ ሆነዋል።
አጥናፍ አምኃ በሙያው የፕሮግራም አናሊስት ሲሆን የ20 ዓመት ልምድ ባለቤትም ነው። አጥናፍ በዋናነት የሂሳብ፤ ኮምፒውተር ሳይንስና ስታትስቲክስ ሙያዎች ትምህርትን የቀሰመ ሲሆን በማይክሮሶፍት ፓወር ፕላትፎርም መተግበሪያ በሆኑት ሼርፖኢንት፤ ፓወር አፕስና ፓወር ቢ አይ የተካነ እንደሆነ ተነግሯል።
አጥናፍ በየቀኑ በሚሰራቸው የቴክኖሎጂ አገልግሎት መተግበሪያዎች እንደሚደሰት ተናግሯል። የአሌክሳንድሪያ ነዋሪ የሆነው አጥናፍ አክሎም ለህይወቱ ትርጉም በሚሰጡት በባለቤቱና በሁለቱ ልጆቹ መነቃቃትን እንደሚያገኝ ተናግሯል። መረጃውን ያገኘነው ከማህበሩ ድረ-ገጽ ነው።
ስለዲሲ ሜሪላንድና ቨርጂንያ በርካታ አዳዲስ መረጃዎችን ለማግኘትና የኢትዮጲክ ዲጂታል ጋዜጣ በኢሜይልዎ እንዲደርስዎት ይህን ሊንክ ተጭነው ይመዝገቡ
ለዲሲ የአመቱ ምርጥ በጎ ፈቃድ ጥቆማ መስጠት ተጀመረ
የዲሲ ከንቲባ ሚውሪየል ባውዘር ማህበረሰባቸውን በበጎ ፍቃድ በማገልገል ላቅ ያለ ሚና ተጫውተዋል ለሚሏቸው ግለሰቦችና ድርጅቶች ዕውቅናና ሽልማት ለማበርከት እንዳቀዱ ዛሬ አሳውቀዋል። ነዋሪዎች ይህ ሽልማት ይገባቸዋል የሚባሉ ግለሰቦችንና ድርጅቶችን እንዲጠቁሙም ጥሪ አቅርበዋል። እናንተም እኛን ኢትዮጲክን ጨምሮ ሌሎች ይገባቸዋል፤ የበጎ ፍቃድ አገልግሎታቸው አርኪ ነው የምትሏቸውን ግለሰቦች ወይንም ተቋማት ካሉ ከስር ባለው ሊንክ ገብታችሁ ጥቆማችሁን ማስገባት ትችላላችሁ።