12/12/2024

የሜሪላንድ ጤና ቢሮ ዛሬ ሐሙስ ኦገስት 18 ባወጣው መግለጫ በካፒታል ሪጅን አካባቢ ያለ የሜሪላንድ ነዋሪ በወባ በሽታ እንደተያዘና ይህ ግለሰብ በቅርብ ጊዜ ምንም አይነት የአገርውስጥም ይሁን የውጭ ሀገር ጉዞ እንዳላደረገና በሽታው እዚሁ እንደያዘው ተነግሯል፡፡ ይህም ከ40 አመት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የወባ በሽታ እዚሁ ባሉ ቢምቢዎች መተላለፍ እንደጀመረ ማሳይ ነው ተብሏል፡፡

በአመት እስከ 2000 የወባ በሽተኞች በአሜሪካ እንደሚያዙ መግለጫው አሳውቋል፡፡ ሆኖም አብዛኞቹ በበሽታው የሚያዙት ከአሜሪካ ውጪ ባሉ ሀገራት በሚያደርጓቸው ጉዞዎች በሽታው እንደሚይዛቸው ይታወቃል፡፡ ሜሪላንድ በአመት በአማካይ እስከ 200 ያህል የወባ በሽታ የያዛቸው ሰዎችን የምታስተናግድ ሲሆን ሁሉ ታዲያ ከሌላ አገር ይዘውት እንደሚመጡ ተነግሯል፡፡

ባለሞያዎቹ አክለውም የቢምቢ መከላከያዎችን መጠቀምና ከቢንቢ ንክሻ የሚከላከሉ ረጃጅምና ሰፋፊ ልብሶችን መልበስና ሌሎች ከስር የተቀመጡ የመፍትሄ ኃሳቦችን ጨምረዋል፡፡

ወባ በተደጋጋሚ በሚከሰትበት አካባቢ የምትኖር ከሆነ . . .

  • አጎበር ተጠቀም። አጎበሩ
    • የተባይ ማጥፊያ የተረጨበት
    • ምንም ቀዳዳ የሌለው
    • በፍራሹ ዙሪያ የተጠቀጠቀ መሆን አለበት።
  • ቤት ውስጥ የሚረጭ የተባይ ማጥፊያ ተጠቀም
  • የሚቻል ከሆነ በበሮቹና በመስኮቶቹ ላይ እንደ ወንፊት ያለ መከለያ አድርግ፤ እንዲሁም ትንኞች እንዳያርፉ ሊከላከሉ ስለሚችሉ እንደ አየር ማቀዝቀዣ ያሉ መሣሪያዎችን ተጠቀም።
  • ሰውነትህን ሙሉ በሙሉ የሚሸፍን ነጣ ያለ ቀለም ያለው ልብስ ልበስ።
  • የሚቻል ከሆነ የወባ ትንኞች በብዛት ከሚገኙበት ጥሻ የሆነ አካባቢና ለትንኝ መራቢያነት አመቺ የሆኑ የታቆሩ ውኃዎች ካሉበት ቦታ ራቅ።
  • በወባ ከተያዝክ በአፋጣኝ የሕክምና እርዳታ ለማግኘት ጥረት አድርግ።

መረጃውን ያገኘነው ከሜሪላንድ ጤና ቢሮ ድረገጽ ነው፡፡

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት