የአሜሪካ ሸማቾችና ምርቶች ደህንነት ኮሚሽን ከትላንት በስትያ ኦገስት 17 ባወጣው መግለጫ ኮስኮ ሲሸጣቸው የከረሙት ባለ አንድና ባለሁለት ዩቢዮ ላብስ የተባለ ፓወር ባንክ ከልክ በላይ በመሞቅና እሳት በመፍጠሩ ምክንያት ምርቱን የገዙ የኮስኮ ደንበኞች ባስቸኳይ እንዲመልሱና ገንዘባቸውን እንዲመለስላቸው ታዟል።
ተመላሽ እንዲሆኑ የተወሰነባቸው ፓወር ባንኮች ጥቁር ቀለም ያላቸውና ከጀርባቸው የሞዴል ቁጥር PWB1071 የተጻፈባቸው ናቸው።
የዚህ ፓወር ባንክ አምራች በጠቅላላው 350000 ምርቶቹን ለገበያ አቅርቦ ነበር። አምራቹ በአሁኑ ሰዓት ስራ አቁሟል። በነዚህ የፓወር ባንኮች የተነሳ 3 አደጋዎች እንደደረሱ ኮስኮ አስታውቋል። ከነዚህም አንዱ በመንገደኞች አውሮፕላን ላይ እንደሆነ ተነግሯል።
ሙሉ ዜናውን ለማየት ይህን ይጫኑ
ስለዲሲ ሜሪላንድና ቨርጂንያ በርካታ አዳዲስ መረጃዎችን ለማግኘትና የኢትዮጲክ ዲጂታል ጋዜጣ በኢሜይልዎ እንዲደርስዎት ይህን ሊንክ ተጭነው ይመዝገቡ
ለዲሲ የአመቱ ምርጥ በጎ ፈቃድ ጥቆማ መስጠት ተጀመረ
የዲሲ ከንቲባ ሚውሪየል ባውዘር ማህበረሰባቸውን በበጎ ፍቃድ በማገልገል ላቅ ያለ ሚና ተጫውተዋል ለሚሏቸው ግለሰቦችና ድርጅቶች ዕውቅናና ሽልማት ለማበርከት እንዳቀዱ ዛሬ አሳውቀዋል። ነዋሪዎች ይህ ሽልማት ይገባቸዋል የሚባሉ ግለሰቦችንና ድርጅቶችን እንዲጠቁሙም ጥሪ አቅርበዋል። እናንተም እኛን ኢትዮጲክን ጨምሮ ሌሎች ይገባቸዋል፤ የበጎ ፍቃድ አገልግሎታቸው አርኪ ነው የምትሏቸውን ግለሰቦች ወይንም ተቋማት ካሉ ከስር ባለው ሊንክ ገብታችሁ ጥቆማችሁን ማስገባት ትችላላችሁ።