የሞንትጎመሪ ካውንቲ ታዳጊዎች በሚያሽከረክሩበት እና በሚራመዱበት ወቅት ሞባይል ስልኮች ትኩረታቸውን እንዳይከፋፍሉ ለማበረታታት ታዳጊዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ቪዲዮዎችን በማዘጋጀት የሚሳተፉበትን ውድድር አዘጋጅቷል። የካውንቲው የትራንስፖርት ዲፓርትመንት የግልና የህዝብ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች በዚህ የቪዲዮ ውድድር እንዲሳተፉ የጠየቁ ሲሆን ውድድሩ ከፌብሩዋሪ 1 እስከ ፌብሩዋሪ 22 መካከል የ30 ሰከንድ የቪዲዮ ማስታወቂያዎችን ይቀበላል።
የሞንትጎመሪ ካውንቲ የህዝብ እና የግል ሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ቪዲዮዎችን ለውድድሩ ማስገባት ይችላሉ። የቪዲዮ ማስታወቂያዎቹ በተናጥል ወይም በቡድን እስከ አራት የሚደርሱ ታዳጊዎች በእንግሊዝኛ ወይም በስፓኒሽ ሊያቀርቡ ይችላሉ።
ይህ የአቻ ለአቻ የደህንነት ጥበቃ ድጋፍ ሁሉም ሰው፣ አሽከርካሪዎች እና መራመጃዎች ነቅተው እንዲቆዩ እና በሚጓዙበት ጊዜ ትኩረታቸውን እንዳይከፋፍሉ ግንዛቤን ለማሳደግ ይረዳል። ይህ ውድድር በመንገድ ላይ ትኩረትን የሚከፋፍሉ አጋጣሚዎችን በማስወገድ እና የእግረኞችን ደህንነት ለመጨመር ያሰበና የካውንቲውን ቪዥን ዜሮ ግቦችን ለማገዝ ይረዳል ተብሏል።
በግለሰብ እና በቡድን የማስረከቢያ ምድቦች ከአንድኛ እስከ ሶስትኛ ለሚወጡ በየደረጃው ሽልማት ይኖራል። የቡድን ተወዳዳሪ አሸናፊዎች ለእያንዳንዱ አባል ጊፍት ካርዶች ይከፋፈላል። የግል ተወዳዳሪ አሸናፊዎች ደግሞ PlayStation Fiveን ጨምሮ የአፕፕል ዋች/ሰዓትና የትራይፖድ ሽልማት ሊወስዱ ይችላሉ።
ተማሪዎች እዚህ በድረ-ገጹ የመግቢያ ቅጽ ላይ ያለውን ቅጽ በመሙላት በውድድሩ መሳተፍ ይችላሉ ።
አሸናፊ ተማሪዎ አርብ ማርች 11 ከቀኑ 5 ሰአት ላይ በ Instagram ላይ በቀጥታ እና እዚህ በኤምሲዲኦቲ ድረ ገጽ ላይ ይለጠፋሉ ።
ለበለጠ መረጃ የውድድሩን ድህረ ገጽ ይጎብኙ https://www.montgomerycountymd.gov/DOT-PedSafety/HUPD/
ከውድድር ጋር የተያያዙ ጥያቄዎችን ወደ pedestrian.safety@montgomerycountymd.gov ይላኩ።