የዲሲ የውኃና ፍሳሽ ባለስልጣን ትላንት ባወጣው መግለጫ በትላንትናው ዕለት የቧምቧ ውኃ ግፊት የቀነሰባቸው ነዋሪዎች በተለይም በከተማው የሰሜን ምስራቅ አካባቢ ያሉ ደንበኞች የቧንቧ ውኃ ለመጠጥም ይሁን ለምግብ መስሪያ ከመጠቀማቸው በፊት ውኃውን እንዲያፈሉት ተመክሯል። በዚህ መግለጫ የውኃ መበከል ያሰጋቸዋል የተባሉት ሰፈሮች የዲሲ ኮስትኮ የሚገኝባቸው ምስራቃዊ ጫፍ ያሉት እንደ ፎርት ሊንከን፤ ውድብሪጅ እና ላንግደን ናቸው። በዋናነትም ይህ የውኃ መበከል ስጋት ከሞንታና አቬኑ በስተምስራቅ፤ ከኢስተርን አቬኑ በስተምዕራብ፤ ከሮድ አይላንድ አቬኑ በስተደቡብና ከኒው ዮርክ አቬኑ በስተሰሜን ያለውን የዲሲ ግዛት ያጠቃልላል።
ለበለጠ መረጃም የዲሲ የውኃና ፍሳሽ ባለስልጣን ነዋሪዎች ይህን ሊንክ በመከተልና የመኖሪያ አድራሻቸውን በማስገባት ወይንም በስልክ ዉጥር (202) 612-3400 በመደመወል ይህ መግለጫ የመኖሪያ ሰፈራቸውን ይመለከት እንደሆነ ማወቅ ይቻላል ብሏል።
ከላይ ከተጠቀሱት አካባቢዎች ውጭ ያሉ ነዋሪዎች ያለምንም ስጋት የቧንቧ ውኃ መጠቀም እንደሚችሉ የዲሲ ውኃ አስታውቋል። በቀጣይ የላቦራቶሪ ምርመራ ውሃው ለመጠጥ ደህንነቱ የተጠበቀ መሆኑን እስካልተረጋገጠ ድረስ ይህ ምክር እንዳለ ይቆያል።
በነዚህ አካባቢዎች ያሉ ነዋሪዎች ምን ማድረግ ይጠበቅባቸዋል?
- በቧንቧ ውኃ የተሰሩ በረዶዎችንና ሌሎች መጠጦችን ያስወግዱ
- ውኃ ከቧንቧ ሲወርድ ቀለሙን ከቀየረ ንጹህ ውኃ መፍሰስ እስኪጀምር ቧንቧውን ከፍተው ይተዉት
- የታወቁ የሊድ ምንጮች ካሉ ቀዝቃዛ ውኃ ለሁለት ደቂቃ ያፍሡ
- ውኃውን ቢያንስ ለ1 ደቂቃ በደንብ ያፍሉትና አቀዝቅዘው ይጠቀሙ
- የቀዘቀዘውን ውኃ በንጹህና በተሸፈነ ማስቀመጫ ያኑሩት
በዚህ ወቅት ፈልቶ የቀዘቀዘ ውሃ ወይም የታሸገ ውሃ ብቻ ለሚከተሉት አገልግሎቶች ጥቅም ላይ መዋል አለበት፡-
- ለመጠጥ
- ጥርስ ለመቦረሽ
- ምግብ ለማብሰል እና ማዘጋጀት
- ፍራፍሬዎችን እና አትክልቶችን ለማጠብ
- የሕፃናት ፎርሙላ ለማዘጋጀት
- በረዶ ለመሥራት
- ለቤት እንስሳት የመጠጥ ውሃ ለመስጠት
በፍጹም የውኃ ማጣሪያ ማሽኖችን ብቻ ተማምነው ውኃ ከማፍላት እንዳይዘናጉ።
ምን ተፈጥሮ ነው ይሄ ማስጠንቀቂያ የወጣው?
እሁድ ግንቦት 28 ቀን 2023 ምሽት ላይ የዲሲ ውሃና ፍሳሽ ዝቅተኛ ወይም ምንም የውሃ ግፊት የለንም ከሚሉ ደንበኞች በሰሜን ምስራቅ ዲሲ ውስጥ ከሚኖሩ በርካታ ጥሪዎችን ተቀበለ። የዲሲ ውሃና ፍሳሽ አሁንም መንስኤውን በማጣራት እና የውኃ ግፊትን ለመመለስ እየሰራ ነው. በስርአቱ ውስጥ ያለው ግፊት በመጥፋቱ ባክቴሪያ ወይም ሌሎች በሽታ አምጪ ተህዋሲያን በማከፋፈያ ስርዓቱ ውስጥ ባሉ ስንጥቆች፣ ስብራቶች ወይም መገጣጠሚያዎች ወደ ውሃ ውስጥ ሊገቡ ይችላሉ።
እንደ ባክቴሪያ፤ ቫይረሶች እና ጥገኛ ተህዋሲያን ያሉ እና ሌሎች በሽታ አምጪ ብክለት እንደ ተቅማጥ፣ ቁርጠት፣ ማቅለሽለሽ፣ ራስ ምታት ወይም ሌሎች ምልክቶችን ሊያስከትሉ ይችላሉ። ለጨቅላ ሕፃናት፣ ለታዳጊ ሕፃናት፣ ለአንዳንድ አረጋውያን እና በጣም የተዳከመ የበሽታ መቋቋም ሥርዓት ላላቸው ሰዎች የከፋ የጤና አደጋ ሊያስከትሉ ይችላሉ።
ከላይ ያሉት ምልክቶች የሚከሰቱት በመጠጥ ውሃ ውስጥ በሚገኙ ማይክሮቦች ብቻ አይደለም. ከእነዚህ ምልክቶች ውስጥ አንዳቸውም ካጋጠሙዎት እና ከቀጠሉ የሕክምና አገልግሎት ያግኙ። ለአደጋ የተጋለጡ ሰዎች ስለ መጠጥ ውሃ ከጤና አጠባበቅ አቅራቢዎቻቸው ምክር ማግኘት አለባቸው።
የዲሲ ውኃ በአሁኑ ሰዓት ውሃው በዚህ ክስተት መበከሉን ምንም መረጃ የለንም ሲል ነገርግን ለጥቃቄ ሲባል ይህ መግለጫ እንደወጣ አስታውቀዋል። በቀጣይም የዲሲ ውኃና ፍሳሽ ባለሞያዎች በተጎዳው አካባቢ የተለያዩ ናሙናዎችን በመሰብሰብ በዕርግጥም ውኃው መበከልና አለመበከሉን የማጣራት ስራ ይሰራሉ። በተከታታይ ሁለት ቀናት በተደረጉ ምርመራዎችም በሽታ አማጭ ጀርሞች ካልተገኙ ማስጠንቀቂያው የሚነሳ ሲሆን ይህም ምናልባት ማክሰኞ ሜይ 30 ሊሆን እንደሚችል መግለጫው አሳውቋል።
ከላይ በተጠቀሱት አካባቢዎች የሚኖሩ ወዳጅ ዘመዶች ካሏችሁ ራሳቸውን ከበሽታ እንዲጠብቁ ይህን መረጃ አጋሯቸው።