የሪፐብሊካኑ የቨርጂንያ ስቴት ገዢ የግሌን ያንግኪን ሞዴል ፖሊስ የሆነውና ጾታቸውን በቀየሩ ተማሪዎች ላይ የሚያተኩረው ረቂቅ ፖሊሲ የአገሪቱን ህገመንግስት እንደማይጋፋና የስቴቱ ትምህርት ቦርዶች በሙሉ ሊተገብሩት እንደሚገባ የቨርጂንያ አቃቤ ህግ ጄሰን ሚያሬዝ ዛሬ ሐሙስ ኦገስት 24 2023 አስታውቀዋል ሲል አሶሼትድ ፕሬስ ዘግቧል።
እንደ ዘገባው ከሆነ አቃቤ ህጉ ይህ ሞዴል ፖሊሲ ሁሉንም ተማሪዎች ሳያበላልጥ በአንድ አይን የሚያይና በዋናነት ደሞ ወላጆች በልጆቻቸው ላይ ያላቸውን መብትና ውሳኔ የሚያከብር በመሆኑ ሁሉም የትምህርት ቦርዶች ሊተገብሩት ይገባል ብለዋል።
የአቃቤ ህግ ጄሰን ሚያሬዝ ምክራዊ ኃሳብ በተለይም በርካታ የቨርጂንያ ስቴት ትምህርት ቦርዶች የገቨርነር ያንግኪንን ውሳኔ እንደማይቀበሉና ተግባራዊ እንደማያደርጉ እያስታወቁ ባሉበት ሰዓት የወጣ ምክረ-ኃሳብ ነው።
በግሌን ያንግኪን አዲስ ፖሊሲ መሰረት ተማሪዎች የሚጠሩት ሲወለዱ በነበራቸው ጾታ እንደሆነና፤ መቀየር ከፈለጉም የወላጆቻቸው ይሁንታ የግዴታ መጠየቅ እንዳለበት ያትታል። በተጨማሪም ማንኛውም ጾታ የቀየረ ሰው በስፖርታዊ ውድድሮች ሲወለድ በነበረው ጾ ታ ብቻ እንዲሳተፍ ያዛል።
የዛሬውን የአቃቤ ህግ ምክረኃሳብ የቨርጂንያ ገቨርነር ግሌን ያንግኪን በደስታ እንደተቀበሉትና በልጆች ጉዳይ ያለውን መብት ወደወላጆች መልሶ የሚሰጥ ነው ሲሉ አሞካሽተውታል።
ሙሉውን የአሶሼትድ ፕሬስ ዘገባ ለማየት ይህን ይጫኑ።
በአካባቢዎ ባሉት ማህበራዊ ፤ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ይሳተፉ። እስካሁን ካልተመዘገቡ ለ2024 አገር ዓቀፍ ምርጫ መመዝገብዎንና በምርጫ መሳተፍዎን አይርሱ። እንደመኖሪያዎ ከስር ያሉትን ተጭነው ይመዝገቡ