12/12/2024
Add-a-heading2

በንብ እርባታ መሳተፍ ለሚፈልጉና ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በላይ የሆኑ የቨርጂንያ ነዋሪዎች በሙሉ ከዛሬ ኦገስት 28 ጀምሮ እስከ ሴፕቴምበር 12 2023 በሚቆየው የምዝገባ ወቅት በመመዝገብ የንብ ቀፎ ባለቤት ለመሆን የሚወጣው የሎተሪ ዕጣ መሳተፍ ይችላሉ፡፡

የዚህ ሎተሪ አሸናፊዎች የወሰዱትን የንብ ቀፎ በአንድ አመት ውስጥ ገጣጥመው በጥቅም ላይ ማዋል ይኖርባቸዋል፡፡ በዚህ ፕሮግራም አሸንፈው የንብ ቀፎ የሚወስዱ ነዋሪዎች በቨርጂንያ ግብርና ቢሮ በንብ አርቢነት ይመዘገባሉ፡፡

የዚህ ፕሮግራም አሸናፊዎች ንግስቲቷን ንብና ሌሎች ለንብ እርባታ የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶችን ራሳቸው እንዲያቀርቡ ይጠበቅባቸዋል፡፡

ማንኛውም በዚህ ፕሮግራም መሳተፍ የሚፈልግ ሰው በዚህ ሊንክ መመዝገብ ይችላል፡፡ አልያም ይህን ፎርም ፕሪነት አርጎና ሞልቶ ከስር ባለው አድራሻ ከሴፕቴምበር 12 2023 በፊት መላክ ይኖርበታል፡፡

በዚህ አድራሻ ይላኩ

Virginia Department of Agriculture and Consumer Services

Office of Plant Industry Services

ATTN: Beehive Distribution Program

PO Box 1163,

Richmond, Virginia, 23218

ለበለጠ መረጃ ይህን ሊንክ ተጭነው ይሂዱ

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት