12/12/2024
Add a heading (11)

ዛሬ ሐሙስ ኦገስት 24 2023 ተሰይሞ በዋለው የችሎት ውሎና በተለይም የካውንቲው ወላጆች ልጆቻቸውን ከተመሳሳይ ጾታ ገጸ-ባህርያት ካሉባቸው መጽኃፍት ንባብ ልጆቻቸውን እንዳያስወጥ ወስኗል።
ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውይንን ጨምሮ ሌሎች ቤተሰቦች በተሳተፉባቸው የተቃውሞ ሰልፎች ላይ የተንጸባረቁትና ወላጆች በአንደኛው የአሜሪካ ህገ-መንግስት ማሻሻያ የተጠቀሰውን የኃይማኖት ነጻነት ይጋፋል ባሉት በዚህ አስተምህሮ ላይ ወላጆች ልጆቻቸውን ማስወጣትን እንደ አማራጭ እንዲኖር የጠየቁ ቢሆንም፤ የካውንቲው የትምህርት ቦርድና ባለስልጣናት ግን ወላጆች ልጆቻቸውን ከነዚህ ትምህርቶች ማስወጣት እንደማይችሉ ሲናገሩ ቆይተዋል። ይህን ተከትሎም የተወሰኑ ወላጆች ጉዳዩ ወደፍርድ ቤት የወሰዱት ሲሆን ፍርድ ቤትም ወላጆች ልጆቻቸውን ከነዚህ ትምህርቶች ማስወጣት እንደማይችሉ ዛሬ የተሰየሙት የፌደራል ዳኛ ዴብራ ቦርድማን ፈርደዋል ሲል ዋሽንግተን ፖስት ዘግቧል።
በሜሪላንድ ህግ ተማሪዎች የተወሰኑ ትምህርቶች ላይ ያለመሳተፍ መብት አላቸው። ከነዚህም በኃይስኩል የሚሰጡት ስለ ቤተሰባዊ ህይወትና የሰው ስነ-ጾታን የያዙ ትምህርቶች ዋነኞቹ ናቸው። ሆኖም አሁን በንባብና በአርት መልክ የመጡት መጽኃፎች ስለተመሳሳይ ጾታ የሚተርኩ ሆነው ሳለ ለኃይስኩል ተማሪዎች እንደምርጫቸው የሚሰጡ ትምህሮች ለኤለመንተሪ ተማሪዎች ግዴታ መሆናቸው ተገቢ እንዳልሆነ የከሳሽ ቤተሰቦች ጠበቃ የሆኑት ኤሪክ ባክስተር ተናግረዋል።
ዝርዝር የዋሽንግተን ፖስትን ዘገባ ይህን ሊንክ ተከትለው በመሄድ ያገኙታል።


በአካባቢዎ ባሉት ማህበራዊ ፤ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ይሳተፉ። እስካሁን ካልተመዘገቡ ለ2024 አገር ዓቀፍ ምርጫ መመዝገብዎንና በምርጫ መሳተፍዎን አይርሱ። እንደመኖሪያዎ ከስር ያሉትን ተጭነው ይመዝገቡ

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት