12/12/2024
Maryland Homeowner Assistance Fund

የሜሪላንድ የቤት ባለቤት እርዳታ ፈንድ ሞርጌጅ መክፈል ላልቻሉ፣ ለሆም ኦውነር አሶሲዬሽን እዳ፤ የሪል እስቴት ታክሶች እና ሌሎች እርዳታዎችን ወይም ብድርን ሊሰጥ ይችላል።

የቤት ባለቤቶች ድጋፍ ፈንድ (Homeowner Assistance Fund) በማርች 11፣ 2021 በወጣው የአሜሪካ የነፍስአድን እቅድ ህግ (American Rescue Plan Act) መሰረት የተቋቋመና ከጃንዋሪ 21፣ 2020 በኋላ በተለያየ ምክንያት የገንዘብ እጥረት ያጋጠማቸውን የሜሪላንድ የቤት ባለቤቶችን ለመርዳት ያቀደ ፕሮግራም ነው። የሜሪላንድ የቤቶች እና የማህበረሰብ ልማት ዲፓርትመንት በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት ከቤት ማስያዣ ክፍያ ወይም ከሌሎች የቤት ወጪዎች ጋር የሚታገሉ የቤት ባለቤቶችን ለመርዳት በዚህ ፕሮግራም በሶስት ዓመታት ውስጥ 248 ሚሊዮን ዶላር ይወስዳል። መርሃግብሩ ከአጭር ጊዜ ርዳታ በተቃራኒ የረጅም ጊዜ ዘላቂ እና ተመጣጣኝ ብድር ይፈጥራል ። ለበለጠ መረጃ ይህን ይመልከቱ።

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት