12/12/2024


የMontgomery County Health and Human Services (DHHS) ለ 2023 የበጀት ዓመት (እ.ኤ.አ. 2023) የማህበረሰብ አገልግሎት ላይ ለተሰማሩና ለትርፍ ላልተቋቋሙ ድርጅቶች ለሚያደርገው የድጋፍ ፕሮግራም ማመልከቻዎችን እየተቀበለ ነው።
ደህንነቱ የተጠበቀ፣ ጤናማ እና እራሱን የቻለ ማህበረሰብን የሚያበረታቱ የጤና እና የሰብአዊ አገልግሎት ፕሮጀክቶችን ለመደገፍ እስከ 10,000 ዶላር የሚደርስ እርዳታ የተዘጋጀ ሲሆን መምሪያው (DHHS) ሁሉንም የቀረቡትን ማመልከቻዎች ይገመግማል። በዋናነትም ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ ጋር በቀጥታ ለሚሰሩ ፕሮጀክቶች ቅድሚያ የሚሰጥ ይሆናል።
በውድድሩ ለመሳተፍ የማመልከቻዎች የማቅረቢያ ቀነ-ገደብ አርብ፣ ጥር 28፣ 2022 ቀን 5፡00 ፒ.ኤም ነው።
የማመልከቻ ፎርምና ተጨማሪ መረጃዎች በዚህ ሊንክ ያገኛሉ። DHHS website under the subheading, “Hot Topics.” 
የዲኤችኤችኤስ ዳይሬክተር ዶ/ር ሬይመንድ ክሮዌል አክለው እንዳሉት “እነዚህ ድጋፎች በዋናነት ጎረቤቶችን በማብቃት ጎረቤቶችን ለመርዳት ያለሙ ናቸው” ብለዋል። አክለውም “በማህበረሰባችን ውስጥ ያለው የፍላጎት ማሻቀብ በወረርሽኙ በጣም በተባባሰበት በዚህ ወቅት፣ ይህ የገንዘብ ድጋፍ የካውንቲያችንን ጠንካራ የማህበራዊ ደህንነት መዋቅር ለማጠናከር ረጅም መንገድ እንደሚሄዱ በማወቄ ኩራት ይሰማኛል።”
ይህ ፕሮግራም የሞንትጎመሪ ካውንቲ ነዋሪዎችን ለሚያገለግሉ ለትርፍ ያልተቋቋሙ ድርጅቶች የአንድ ጊዜ ብቻ ድጎማ ይሰጣል። አሸናፊ ድርጅቶችም ለተፈቀዱ መሳሪያዎች እና ሌሎች የካፒታል ግዢዎች ክፍያን እንዲያስፈፅሙ ይረዳል።
ለበለጠ መረጃ ወደ  Community.ServicesGrants@montgomerycountymd.gov ኢሜይል ይላኩ ።

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት