12/12/2024
መልካም ኦክቶበር ይሁንላችሁ!!

በኦኮኳን ግድብ አቅራቢያ ለሚኖሩ ሰዎችና በአካባቢው ላሉ የንግድ ተቋማት፤ ድንገት ግድቡ ተደርምሶ አደጋ ቢደርስ ማስጠንቀቂያ የሆነው ሳይረን ነገ ኖቨምበር 14 2023 ከጠዋቱ 10 ሰዓት ላይ ይጮኃል ሲል የየፌርፋክስ ካውንቲ ውኃ ስራዎች አስታውቋል፡፡

ይህ ድምጽ ይሰማባቸዋል የተባሉት አካባቢዎች በግድቡ ዙሪያ ያሉየፕሪንስ ዊልያምና የፌርፋክስ ካውንቲ የሚገኙ ከተሞችና መንደሮችን በሙሉ ያካትታል፡፡ በተጨማሪም የሪጅናል ፓርኩንና ማሪናዎችን ያካትታል፡፡

የሳይረኑን ድምጽ መስማት ከፈለጉ ከስር ያለውን ማጫወቻ ፕሌይ ይበሉ

ግድቡ ከተደረመሰ ሊጎዱ ይችላሉ ያላቸውን አካባቢዎች የካውንቲው መንግስት በማፕ ለይቶ ያስቀመጠ ሲሆን ሳይረኑን የሰሙ ሰዎች ወይንም የሳይረኑ ድምጽ የደረሰባዎች ቦታዎች በሙሉ ግን በዚህ ላይጎዱ እንደሚችሉ ጨምረው ገልጸዋል፡፡ ማፑን ይመልከቱ

በነገው እለት የሚደረገው የሙከራ ማስጠንቀቂያ እንደሆነና ነዋሪዎች ምንም ማድረግ እንደማይጠበቅባቸው ነገር ግን ይህን የሳይረን ድምጽ በሌላቀን ከሰሙ የግድቡ ውኃ ጎርፍ ሆኖ የሚያስከትለውን አደጋ ለማምለጥ በተቻለ ፍጥነት ወደ ተራራማ/ከፍታ ቦታ መሸሽ እንዳለባቸው ተገልጿል፡፡

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት